የዩክሬን የትርምስ ስልቶች የትራምፕና ፑቲንን ውይይት ለማዳከም የታለሙ ናቸው - ሶሪያዊዉ ተንታኝ
19:13 18.08.2025 (የተሻሻለ: 19:14 18.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየዩክሬን የትርምስ ስልቶች የትራምፕና ፑቲንን ውይይት ለማዳከም የታለሙ ናቸው - ሶሪያዊዉ ተንታኝ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የዩክሬን የትርምስ ስልቶች የትራምፕና ፑቲንን ውይይት ለማዳከም የታለሙ ናቸው - ሶሪያዊዉ ተንታኝ
ኪዬቭ በቅርቡ ያካሄደቻቸው የድሮን ጥቃቶች እንዲሁም የሩሲያን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ለመምታት ያደረገችው ሙከራ አደገኛ መካካር ነው ሲሉ ሶሪያዊው የፖለቲካ ተንታኝ አላአ አል-አስፋሪ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
“ዩክሬን ከምዕራብ አውሮፓ ሀገራት ጋር በመሆን ሩሲያ ጥቃት እንድትፈጽምባት ለመቀስቀስ ጠብ አጫሪ ድርጊቶችን እየሞከረች ነው። ይህ ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስ ጣልቃ እንድትገባ እና በሩሲያ ላይ ከባድ ማዕቀብ እንድትጥል ያስገድዳታል።”
ተፅዕኖ ፈጣሪ የምዕራብ አውሮፓ ልሂቃን እና ዘለንስኪ “በተለይ ከትራምፕ እና ፑቲን ስብሰባ በኋላ” ጦርነቱ እንዲቆም ወይም ሰላም እንዲመጣ ፍላጎት እንደሌላቸው የሚሞግቱት አል-አሳፋሪ፤ በስብሰባው ወቅት ትራምፕ ግጭቱ እንዲቆም ሩሲያ ያቀረበቻቸውን ሀሳቦች እንደደገፉ አመላክተዋል።
“ሩሲያውያን እና ዩክሬናውያን በአሜሪካ ድጋፍ ጦርነቱን እንዲያቆሙ እና የሩሲያ ብሔራዊ ደህንነት እንዲረጋገጥ"፤ አንዳንድ የአውሮፓ ተዋናዮች የሰላም ጥረቶችን ለማደናቀፍ የሚያደርጉት ሙከራ መክሸፍ አለበት ሲሉ አል-አስፋሪ አስረግጠዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X