- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

የፑቲን እና ትራምፕ ስብሰባ መልዕክት ፦ ዓለም በባለብዙ ዋልታ ማዕቀፍ

የፑቲን እና ትራምፕ ስብሰባ መልዕክት ፦ ዓለም በባለብዙ ዋልታ ማዕቀፍ
ሰብስክራይብ
“ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ይልቅ ፕሬዝዳንት ፑቲን ያሸነፉ ይመስለኛል። ትራምፕ በድጋሚ ከተመረጡ በኋላ ዩክሬንን በተመለከተ የታዘብነው አንድ ነገር፣ በምዕራባውያን ኃይላትና አጋራት መካከል ትልቅ ክፍፍል ተፈጥሯል። ቀደም ባሉት ጊዜያት በባይደን አስተዳደር ዘመን አውሮፓውያን ከዋሽንግተን የሚወጣውን ማንኛውንም ነገር በጥብቅ ይከታተሉ ነበር። አሁን ግን ግልጽ ተቃውሞ አይተናል። ዜለንስኪ ቢሆን ፕሬዚዳንት ትራምፕን ይቃረናቸዋል። ስለዚህ አንድ ግልጽ የሆነው ነገር በምዕራባውያን አጋራት መካከል መለያየት ያለ ይመስለኛል " ሲሉ ምሁሩና የፖለቲካ ሳይንቲስቱ ዶ/ር አስናቀ ከፋለ ተናግረዋል።
በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው ኃያላኑ የዓለም መሪዎች ቭላድሚር ፑቲንና ዶናልድ ትራምፕ በአላሳካ ያደረጉት ውይይትን በስፋት ያስቃኛል።
በመሪዎቹ ጉባዔ የተነሱ አንኳር ጉዳዮች፣ የግንኙነታቸው ፖለቲካዊ አንድምታ፣ ከጉባዔው መነሻነት ወደፊት የሚጠበቁ ጉዳዮችና ሌሎች በርካታ ተያያዥ ሀሳቦችን ለመወያየት ምሁሩና የፖለቲካ ሳይንቲስቱ ዶ/ር አስናቀ ከፍለ፣ የታሪክ ምሁርና የፖለቲካ ተንታኝ እንዲሁም ጉምቱው ዲፕሎማት አምባሳደር ጥሩነህ ዜናን እንዲሁም ሱዳናዊው የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ተንታኝ፣ ዲፕሎማትና ጋዜጠኛው መኪ ኤልሞግራቢን ጋብዟቸዋል።
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsAfripodsDeezerPocket CastsPodcast AddictSpotify
አዳዲስ ዜናዎች
0