በፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ በዘለንስኪ እና በአውሮፓ ሕብረት መሪዎች መካከል ስለሚደረገው ስብሰባ የታወቁ ጉዳዮች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ በዘለንስኪ እና በአውሮፓ ሕብረት መሪዎች መካከል ስለሚደረገው ስብሰባ የታወቁ ጉዳዮች
በፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ በዘለንስኪ እና በአውሮፓ ሕብረት መሪዎች መካከል ስለሚደረገው ስብሰባ የታወቁ ጉዳዮች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.08.2025
ሰብስክራይብ

በፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ በዘለንስኪ እና በአውሮፓ ሕብረት መሪዎች መካከል ስለሚደረገው ስብሰባ የታወቁ ጉዳዮች

◻ ዘለንስኪ ዋሽንግተን ዲሲ ገብተዋል።

◻ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከዘለንስኪ ጋር የሚያደርጉት ስብሰባ ዛሬ ምሽት በ2:15 ይጀምራል።

◻ ከአውሮፓ ሕብረት መሪዎች ጋር የሚደረገው ስብሰባ ደግሞ ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ ሊካሄድ ታቅዷል።

◻ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዕለቱን “ትልቅ ቀን” ሲሉ የገለጹት ሲሆን፤ ኋይት ሃውስ በታሪኩ በአንድ ጊዜ ይህን ያህል መሪዎችን አስተናግዶ አያውቅም ሲሉ ተናግረዋል።

◻ በስብሰባው ላይ ይገኛሉ ተብለው ከሚጠበቁት መሪዎች መካከል የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ላይን፣ የጀርመን መራሄ መንግስት ፍሬደሪክ ሜርዝ፣ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር፣ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ፣ የፊንላንድ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ስቱብ እና የኔቶ ዋና ጸሐፊ ማርክ ሩቴ ይገኙበታል።

◻ የአውሮፓ መሪዎች ከዘለንስኪ ጋር ለመገናኘት የጉዞ እቅዳቸውን በፍጥነት ማስተካከላቸው ታውቋል።

◻ የጀርመን መራሄ መንግስት ፍሬደሪክ ሜርዝ ለአራት ሰዓታት ብቻ ለሚቆይ አጭር ጊዜ ዋሽንግተን ዲሲን ለመጎብኘት ማቀዳቸው ተገልጿል።

◻ የአውሮፓ መሪዎች ከኃይት ሃውስ ውይይቶች በፊት ከዘለንስኪ ጋር በዋሽንግተን ዲሲ የቅድመ ዝግጅት ስብሰባ ያደርጋሉ ሲል የአውሮፓ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

◻ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሚደረጉት ጉብኝት ዓላማ ሰላም ማስፈን እንደሆነ አስታውቀዋል።

◻ በአውሮፓ መሪዎች፣ በፕሬዚዳንት ትራምፕ እና በዘለንስኪ መካከል በሚደረገው ድርድር ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የምትሰጠው የደህንነት ዋስትና ሊብራራ ይገባል ሲል የጀርመን መንግሥት አፅንኦት ሰጥቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0