ስፑትኒክ በኢትዮጵያ የሬዲዮ ስርጭት ጀመረ
15:02 18.08.2025 (የተሻሻለ: 15:04 18.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ስፑትኒክ በኢትዮጵያ የሬዲዮ ስርጭት ጀመረ
የስፑትኒክ አፍሪካ ፕሮግራሞች በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ሬዲዮ 99.4 ኤፍ ኤም ለ6 ሚሊየን አድማጮች መቅረብ ጀምሯል፡፡
አድማጮች አሁን በሀገሪቱ አንጋፋው ዩኒቨርሲቲ የሬዲዮ ጣቢያ፤ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ የተዘጋጁ የትንታኔ ፕሮግራሞችን ማድመጥ ይችላሉ።
ስፑትኒክ ዓለም አቀፍ የዜና ወኪል እና የሬዲዮ ማሰራጫ ከ30 ቋንቋዎች በላይ ፕሮግራሞቹን የሚያቀርብ ሲሆን በዓለም ዙሪያ 24 የኤዲቶሪያል ማዕከላት አሉት፡፡
ስፑትኒክ አገልግሎተ ብዙ ኤዲቶሪያል ማዕከሉን በ2025 በአዲስ አበባ ከፍቷል። በአማርኛ ቋንቋ የሚሠራ ብቸኛው የሩሲያ ሚዲያ ነው።
ስፑትኒክ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በሌሎች 7 የአፍሪካ ሀገራት ማለትም በናይጄሪያ፣ ጊኒ፣ ዛምቢያ፣ ካሜሩን፣ ማሊ፣ ኒጀር እና ቦትስዋና ፕሮግራሞቹን ያስተላልፋል።
ስፑትኒክ አፍሪካ፤ የአፍሪካ ብሮድካስቲንግ ኅብረት አባል እና ተሸላሚ ነው፡፡ በአህጉሪቱ ባሕል ዙሪያ በሚያዘጋጃቸው ፕሮግራሞቹ በምርጥ የሬዲዮ መፅሄት እና በምርጥ የሬዲዮ ፕሮግራም ምድቦች የኅብረቱን ሽልማት ተቀዳጅቷል፡፡ ስፑትኒክ ሰሜናዊ አፍሪካን በሚሸፍነው የአረብ ብሮድካስቲንግ ኅብረት አባልም ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X