አልዛይመር፦ የመጀመሪያ ምልክቶች እና ለወደፊት ተስፋዎች
12:45 18.08.2025 (የተሻሻለ: 12:54 18.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አልዛይመር፦ የመጀመሪያ ምልክቶች እና ለወደፊት ተስፋዎች
“ከጭንቀት በኋላ የሚከሰት የመርሳት ችግር አልዛይመር አይደለም። ዋናው ምልክት የሩቅ ጊዜ ትውስታዎች እንዳሉ፤ የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን መርሳት ነው” ሲሉ በሞስኮ ስቴት ሜዲካል ዩኒቨርሲቲ የነርቭ በሽታዎች እና የነርቭ ቀዶ ጥገና ክፍል ኃላፊ ፕሮፌሰር ቭላዲሚር ፓርፌኖቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
በሽታው በዝምታ ከ10 እስከ 20 ሊጎለብት እንደሚችል ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ዘመናዊ ሳይንስ በአከርካሪ አጥንት ፈሳሽ ውስጥ በሚገኙ ባዮማርከሮች በቅርቡ ደግሞ በደም ምርመራ ሊታወቅ ይቻላል ብለዋል።
እንደ ሐኪሙ ገለጻ፤ የአኗኗር ዘይቤ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
ፓርፌኖቭ “የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የአእምሮ ሥራ እንዲሁም በደም ግፊት፣ በስኳር፣ በኮሌስትሮል እና በእንቅልፍ ላይ የሚደረጉ ቁጥጥሮች የመገንዘብ ማሽቆልቆልን በእጅጉ ሊቀንሱ ይችላሉ” ብለዋል።
በሕክምናው ዘርፍ የተመዘገበውን እድገት አስመልክቶም አንስተዋል። “አዲሶቹ መድኃኒቶች ለካኔማብ እና ዶናኔማብ የአልዛይመር በሽታን ከሁለት እስከ ሶስት ዓመት ሊያዘገዩ ይችላሉ።”
ምንም እንኳን ከሽታው የማይድን ቢሆንም አሁን ላይ ታካሚዎች ትርጉም ያለውና ፍሬያማ ሕይወታቸውን ለተጨማሪ ዓመታት ሊያራዝሙ እንደሚችሉ ሩሲያዊው ሐኪም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X