የፑቲን እና ትራምፕ የአላስካ ስብሰባ በመሪዎቹ መካከል መተማመን ለመፍጠር የመጀመርያው እርምጃ እንደሆነ የታሪክ ምሁሩ ገለፁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየፑቲን እና ትራምፕ የአላስካ ስብሰባ በመሪዎቹ መካከል መተማመን ለመፍጠር የመጀመርያው እርምጃ እንደሆነ የታሪክ ምሁሩ ገለፁ
የፑቲን እና ትራምፕ የአላስካ ስብሰባ በመሪዎቹ መካከል መተማመን ለመፍጠር የመጀመርያው እርምጃ እንደሆነ የታሪክ ምሁሩ ገለፁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.08.2025
ሰብስክራይብ

የፑቲን እና ትራምፕ የአላስካ ስብሰባ በመሪዎቹ መካከል መተማመን ለመፍጠር የመጀመርያው እርምጃ እንደሆነ የታሪክ ምሁሩ ገለፁ

መተማመን ከተፈጠረ በኋላ የወደፊት ፕሮግራሞችን መቅረፅ ይችላሉ ሲሉ ምሁሩ ጥላሁን ጣሰው ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት አስተያያት ተናግረዋል፡፡

“ትራምፕ ሩሲያ ጠል አቋሞችን ሲተቹ ማየት ደስ የሚል ነበር፡፡ ፑቲን በአላስካ ባረፉ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት የሩሲያ ጀኞች መካነ መቃብር የአበባ ጉንጉን ማስቀመጣቸው አስደሳች ነበር፡፡ ፑቲንን ከአላስካ የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ኃላፊ ጋር ማየትም እንዲሁ ልብ የሚነካ ነበር” ብለዋል፡፡

የመጨረሻው ውጤት ለሁሉም ግልፅ ነው የሚሉት የታሪክ ምሁሩ፤ በዚህ ሁኔታ በታቸለ ፍጥነት ስምምነት ላይ መድረሱ ይሻላል ብለው እንደሚያስቡ ገልፀዋል፡፡

“ፕሬዝዳንት ትራምፕ በተደጋጋሚ የዩክሬን ጦርነት የእሳቸው እንዳልሆነ እና እሳቸው ፕሬዳንት ሆነው ቢሆን ኖሮ እንደማይፈጠር ይገልፃሉ፡፡ ይህ አቋም አሁንም አልተቀየረም፡፡ አውሮፓ እና ኪዬቭ በተሻለው የአሜሪካ መንገድ ቢጓዙ ይሻላቸዋል፡፡”

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0