ከመጪው መስከረም ጀምሮ ለመንግሥት ተቀጣሪዎች የደሞዝ ማሻሻያ እንደሚደረግ ተገለፀ
10:49 18.08.2025 (የተሻሻለ: 10:54 18.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ከመጪው መስከረም ጀምሮ ለመንግሥት ተቀጣሪዎች የደሞዝ ማሻሻያ እንደሚደረግ ተገለፀ
ለደመወዝ ማስተካከያው ከ160 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት እንደተጠየቀ እና ሀገሪቱ ለደመወዝ የምታወጣውን ጠቅላላ ዓመታዊ የመንግሥት ወጪ 560 ቢሊየን ብር እንደሚያደርሰው የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
በማሻሻያው መሠረት፦
ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከ4 ሺህ 760 ብር ወደ ብር 6 ሺህ፣
ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከ21 ሺህ 492 ብር ወደ ብር 39 ሺህ፣
የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6 ሺህ 940 ወደ ብር 11 ሺህ 500 ያድጋል ተብሏል።
ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝም ማሻሻያ እንደሚደረግበት ተገልጿል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X