የአላስካው ስብሰባ የሩሲያ የታደሰውን ዓለምአቀፍ ተጽዕኖ ያጎላ ነው - ባለሙያ
19:07 16.08.2025 (የተሻሻለ: 19:14 16.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአላስካው ስብሰባ የሩሲያ የታደሰውን ዓለምአቀፍ ተጽዕኖ ያጎላ ነው - ባለሙያ
ስብሰባው ዋሽንግተን “በዩክሬን ግጭት የሩሲያን ድል መቀዳጀት መቀበሏን” ያሳያል ሲሉ የዓለምአቀፍ ጉዳዮች እና የኢነርጂ ጂኦ-ኢኮኖሚክስ ባለሙያው ዶ/ር ሕሪዴ ሳርማ ለስፑትኒክ ገልፀዋል፡፡
በሁለቱም መሪዎች "ፍሬያማ" ከተባለው ስብሰባ በርካታ ቁልፍ ነጥቦችን ጠቅሰዋል፡-
ሩሲያ ለየትኛውም ተዓማኒ የሰላም ሂደት ወሳኝ ሆና ቀጥላለች፡፡
ወሳኙ ውይይት ዩክሬን በሌለችበት በሞስኮ እና በዋሽንግተን መካከል በቀጥታ እየተደረገ ነው፡፡
ሩሲያ በዓለም ጉዳዮች ላይ በተለይም በነዳጅ እና ጋዝ ገበያዎች ውስጥ ወሳኝ ሚና መጫወቷን ቀጥላለች፡፡
ምዕራባውያን ሩሲያን ለማግለል ያደረጉት ጥረት አልተሳካም፡፡
"የአላስካ ስብሰባ ሩሲያ ወደ ዓለምአቀፍ ኃይል ማዕከልነቷ ዳግም መመለሷን አረጋግጧል" ብለዋል፡፡
አሁን ትኩረቶች ሁሉ ወደ በቻይና ቲያንጂ በሚካሄደው መጪው ሻንጋይ የትብብር ድርጅት ጉባኤ ላይ ሆነዋል፡፡ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ተጠባቂ ስብሰባ ደግሞ በዩሮኤሺያ ያለውን የፍተኛ ደረጃ ማዕበል ያስቀጥላል ሲሉ ሳርማ አክለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ |