ሩሲያ እና አሜሪካ በዩክሬን ያለው ፍልሚያ በፍጥነት እንዲያበቃ ይፈልጋሉ - ፑቲን
18:39 16.08.2025 (የተሻሻለ: 18:44 16.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና አሜሪካ በዩክሬን ያለው ፍልሚያ በፍጥነት እንዲያበቃ ይፈልጋሉ - ፑቲን
በሩሲያ እና አሜሪካ ውጤቶችን ውይይት ወቅት የሩሲያ ፕሬዝዳንት የሰጧቸው ቁልፍ መግለጫዎች፦
በአላስካ የተደረጉት ውይይቶች ተሳታፊ ወገኖችን ለአስፈላጊ ውሳኔዎች እያቀራቡ ነው፡፡
አላስካ ሩሲያን አቋሟን በእርጋታ እና በዝርዝር ለማስቀመጥ እድል ሰጥቷል፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ያለው ጦርነት እንዲቆም ትፈልጋለች፤ የቀውሱ መነሻ መንሴዎችን ማስወገድ ለእልባቱ መሠረት መሆን አለበት፡፡
የአላስካ መጎብኘት ወቅታዊ እና በጣም ጠቃሚ ነበር፡፡
የዩክሬንን ቀውስ በፍትሐዊ መንገድ ለመፍታት ውይይት ተድርጓል፡፡
ከትራምፕ ጋር የተደረገው ውይይት ሀቀኛ እና ጠቃሚ ነበር፡፡
ሩሲያ እንደ አሜሪካ ሁሉ የዩክሬን ግጭት በተቻለ ፍጥነት እንዲቆም ትፈልጋለች፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ |