የአላስካ ጉባኤ፦ አውሮፓውያን አሁን የዳር ተመልካች እንደሆኑ መቀበል አለባቸው
16:17 16.08.2025 (የተሻሻለ: 16:24 16.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአላስካ ጉባኤ፦ አውሮፓውያን አሁን የዳር ተመልካች እንደሆኑ መቀበል አለባቸው
በቅርቡ በአላስካ የተካሄደው የትራምፕ እና የፑቲን ስብሰባ "ሁለቱ መሪዎች ለታላላቅ የምዕራቡ ዓለም ሀገራት በተለይም አሁንም ግጭት ለሚመኙ አውሮፓውያን ያስተላለፉት የሰላም ምልክት እና ምሳሌ ነው" ሲሉ ቡርኪና ፋሶዋዊ የፖለቲካ ተንታኝ ሊያንሆው ኢምሆቴፕ ባያላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
"ዩናይትድ ስቴትስ ዛሬ እንዳደረገችው ከአጋሯ ሩሲያ ጋር ከፍተኛ የጂኦፖለቲካዊ ጠቀሜታ ያለው ስትራቴጂያዊ አጀንዳ ለመከተል ያለ አውሮፓውያን መጓዝ መቻል አለባት" ሲሉ አስረግጠዋል።
ተንታኙ ዩክሬን የምዕራቡን ዓለም ተቃውሞ ወደኋላ በማለት፤ የሩሲያን የሰላም ሃሳብ በመቀበል ደህንነቷን ለመጠበቅ እድሉን መጨበት የምትችልበት ወሳኝ ግዜ ላይ ናት ብለዋል።
🟠 ዘለንስኪን "ሕዝቡን በማገት" የከሰሱት ባለሙያው፤ አውሮፓ በግጭቱ ግላዊ ፍላጎቶች እንዳሏት አፅንኦት ሰጥተዋል።
"ጀርመኖች፣ ፈረንሣይ እና በተወሰነ ደረጃ ብሪታንያ በዩክሬን የሚሆነው የሚያስጨንቃቸው በሀገሪቱ ብርቅዬ ማዕድናት ድርሻቸውን ለማስጠበቅ ነው። እውነተኛ ፍላጎታቸው እዚያ ላይ ነው" ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X