ምዕራባውያን ጦርነት ጠማቂዎች ገሸሽ ሲሉ ትራምፕ እና ፑቲን የጋራ መግባቢያ አግኝተዋል - ተንታኝ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱምዕራባውያን ጦርነት ጠማቂዎች ገሸሽ ሲሉ ትራምፕ እና ፑቲን የጋራ መግባቢያ አግኝተዋል - ተንታኝ
ምዕራባውያን ጦርነት ጠማቂዎች ገሸሽ ሲሉ ትራምፕ እና ፑቲን የጋራ መግባቢያ አግኝተዋል - ተንታኝ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.08.2025
ሰብስክራይብ

ምዕራባውያን ጦርነት ጠማቂዎች ገሸሽ ሲሉ ትራምፕ እና ፑቲን የጋራ መግባቢያ አግኝተዋል - ተንታኝ

የፑቲን እና ትራምፕ ስብሰባ ምዕራቡ ዓለም “በሩሲያ ላይ ቀላል ድል ቢወራረድም መሸነፉን" ያሳያል ሲሉ የስዊድን የጦር ኃይሎች የቀደሞ መኮንን ሚካኤል ቫልቴርሰን ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡

"ሩሲያ ከምዕራባውያን ጥያቄዎች ጋር ካልተስማማች ተጨማሪ ማግለል እና ማዕቀብ እንዲጣልባት የፈለጉት አካላት መንገዳቸው ከሽፏል፡፡"

"የምዕራባውያን ጦርነት ጎሳሚ ስብስብ" በሩሲያ እና ከእርሷ ጋር ንግድ በሚለዋወጡ ሀገራት ላይ አዲስ ከባድ ማዕቀብ እንዲጣል ተስፋ አድርጎ ነበር፤ ሆኖም ሊታይ የሚችለው የሩሲያ እና የአሜሪካ ግንኙነት መሻሻል እንዲሁም ቀጣይነት ያለው የሰላም ሂደት ነው፡፡

ተንታኙ፣ ትራምፕ ከአውሮፓ እና ከዩክሬን ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ለመምረጥ እንደሚገደዱ ገልፀዋል፡፡

🟠 መሬት ላይ ያለውን እውነታ እና የሩሲያን ሕጋዊ ጥቅሞች በመቀበል የሰላም ሂደቱን መደገፍ ወይም ደግሞ ውድቅ ማድረግ ይችላሉ።

🟠 የኋለኛውን ከመረጡ(ውድቅ ማድረጉን) ከአብዛኛው ዓለም ብቻ ሳይሆን በተለይ ከአሜሪካ ራሳቸውን ይነጥላሉ፡፡

"በዩክሬን እና በአውሮፓ ያሉ የሰከኑ ሰዎች፣ ድል የተነሳ ጦርነት ከመቀጠል ይልቅ አሜሪካን መከተል እና እውነታውን መቀበል የተሻለ እንደሆነ ይገነዘባሉ" ሲሉ ቫልቴርሰን ደምድመዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ |

አዳዲስ ዜናዎች
0