የትራምፕ እና የፑቲን ስብሰባ፤ ‘የጋራ ራዕይ ምልክት፣ ለሰላም የጋራ ምኞት’

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየትራምፕ እና የፑቲን ስብሰባ፤ ‘የጋራ ራዕይ ምልክት፣ ለሰላም የጋራ ምኞት’
የትራምፕ እና የፑቲን ስብሰባ፤ ‘የጋራ ራዕይ ምልክት፣ ለሰላም የጋራ ምኞት’ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.08.2025
ሰብስክራይብ

የትራምፕ እና የፑቲን ስብሰባ፤ ‘የጋራ ራዕይ ምልክት፣ ለሰላም የጋራ ምኞት’

የአላስካው ስብሰባ ትብብርን የመቀበል ፈቃደኝነትን፣ የቀደሙ ውጥረቶች የማርገብ እንዲሁም ለሩሲያ እና አሜሪካ ስትራቴጂያዊ ምክክር መንገድ ከፋች መሆኑን የቡርኪና ፋሶ የፖለቲካ ተንታኝ ሊያንሁ ኢምሆቴፕ ባያላ ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡

ተንታኙ ሂደቱ ላይ የአውሮፓ ተጽኖ መፍጠር አለመቻልንም ጠቅሰዋል፡፡

“ይህ በዩክሬን ግጭት አቅም ቢስ እና ኃላፊነት የጎደላቸው ሆነው የተገኙትን አውሮፓውያንን ሳያሳትፍ እየሆነ ያለ ነው፡፡” አውሮፓ ወታደራዊ ሉዓላዊነትን እየፈለገች ቢሆንም በኔቶ ጥላ ስር በመሆኗ ሩሲያ እና አሜሪካ በቆረጡ ጊዜ ምንም ተጽዕኖ የሌለው “ማስመሰል” ብቻ መጨረሻዋ እንደሚሆን ባያላ አጽንኦት ሰጥተዋል።"

ባለሙያው፣ ይህንን የግንኙነት መሻሻል ለማደናቀፍ የሚደረጉ ሙከራዎችን እንደሚጠብቁ ቢገልፁም፣ ምንም ሊፈጥሩ አለመቻላቸው ላይ በራስ መተማመናቸው የፀና ነው፡- “የአሻጥር ሙከራዎች እንደሚኖሩ ግልጽ ነው፤ ነገር ግን በእንደዚህ አይነት ጠንካራ ቁርጠኝነትን ፊት እነዚህ ድርጊቶች ምን ሊያሳኩ ይቻላቸዋል?”

የወንድማማችነት እና የጋራ መከባበር ምልክት

ባያላ፣ ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች አንድ መኪና ተጋርተው መታየታቸው “የታላቅነት፣ የአክብሮት እና የጋራ ዓላማ ምልክት ነው” ብለዋል፡፡

“እውነት ነው፣ ያ ምስል የተወሰኑ ምዕራባውያንን አስደስት ይሆናል፡፡ ሆኖም የራሳቸውን ኩራት እና ትዕቢት ብቻ ቢወቅሱ የተገባ ነው፡፡ ምክንያቱም ዛሬ ሰላማዊ ዓለምን ለመገንባት እንደዚህ አይነት አመለካከቶች አያስፈልጉንም” ሲሉ ባያላ አስረግጠዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ለማንበብ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ |

አዳዲስ ዜናዎች
0