በሩሲያ እና በአሜሪካ የሚደረግ ስምምነት ሌሎች ዓለም አቀፍ ስጋቶችን ለመፍታት እንደ ማዕቀፍ ሊያገለግል ይችላል - ባለሙያ
12:44 16.08.2025 (የተሻሻለ: 13:14 16.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበሩሲያ እና በአሜሪካ የሚደረግ ስምምነት ሌሎች ዓለም አቀፍ ስጋቶችን ለመፍታት እንደ ማዕቀፍ ሊያገለግል ይችላል - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሩሲያ እና በአሜሪካ የሚደረግ ስምምነት ሌሎች ዓለም አቀፍ ስጋቶችን ለመፍታት እንደ ማዕቀፍ ሊያገለግል ይችላል - ባለሙያ
የፖለቲካ ሳይንስ እና የዓለምአቀፍ ግንኙነቶች ባለሙያ በፍቃዱ ዳባ፣ ሀገራቱ በወዳጅነት ላይ ተመሥርቶ ጦርነትን ለማቆም በበርካታ ጉዳዮች ላይ በመርህ ደረጃ መስማማታቸውን ገለፀው፣ የመሪዎቹ ዐቢይ ጉዳይ ዓለም አቀፍ የሰላም እና ደህንነትን ጉዳዮች ናቸው ሲሉ ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡
“ለአብነት የኑክሌር ጦር መሣሪያ ውድድርን መቀነስ። ስለዚህ እነዚያን ፍጥጫዎችን ለማርገብ እና እንደገና ወደ ትብብር ለመለወጥ እድል ያገኛሉ። የሁለቱ የሀገር መሪዎች በጣም ተግባቢ ናቸውና እርስ በርስ መግባባት ይችላሉ፡፡”
ዶናልድ ትራምፕ ለፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ እና ለአውሮፓ ዋና ዋና ኃይሎች ወይም ለኔቶ አባላት በመደወላቸው ምክንያት የሆነ አይነት መለሳለስ ሊኖር እንደሚችልም ባለሙያው ጠቁመዋል፡፡
ባለሙያው ስብሰባውን አስመልክቶ ያነሷቸው ተጨማሪ ነጥቦች፦
አሜሪካ የአውሮፓ ሀገራት እንዴት መሆን እንዳለባቸው መንገር ትችላለች፡፡
በዶናልድ ትራምፕ እና በፑቲን ስለሚግባቡ ለችግሮች እልባት አንዳች አይነት የጋራ መግባባት ይፈጥራሉ፡፡
ማዕቀብ ብዙ ሀገራትን አድቅቆ ምቹ ያልሆነ ሁኔታን ፈጥሯል።
ሩሲያ በነዳጅ እና ጋዝ የበለፀገች ሀገር እንደመሆኗ ማዕቀብ የነዳጅ እና ጋዝ ሽያጭ ላይም ተጽዕኖ ፈጥሯል፡፡
የመሪዎቹ ስብሰባ በብዙ መንገዶች ለዓለም ሰላም እና ደህንነት አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ |