በአላስካ የፑቲን መግለጫ ቁልፍ ነጥቦች፡-

ሰብስክራይብ

በአላስካ የፑቲን መግለጫ ቁልፍ ነጥቦች፡-

▪ ፑቲን ከትራምፕ ጋር ያደረጉትን ንግግር ገንቢ እና ጠቃሚ ነው ሲሉ ገልፀውታል።

▪ ፑቲን ሩሲያ እና አሜሪካ ጎረቤቶች በመሆናቸው ጉባኤው አላስካ መደረጉ ምክንያታዊ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

▪ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ከትራምፕ ጋር በአላስካ ሲገናኙ እንደ ጎረቤት ሰላምታ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።

▪ ፑቲን ዩናይትድ ስቴትስ በአላስካ ለተቀበሩት የሶቪየት ወታደሮች መታሰቢያ አክብሮት በመስጠቷ ምስጋና አቅርበዋል።

▪ የሩሲያ እና አሜሪካ ግንኙነት "ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋላ ዝቅተኛው ደረጃ ላይ ደርሷል" ያሉት ፑቲን፤ ከትራምፕ ጋር በጣም ጥሩ የሆነ ቀጥተኛ ግንኙነት መመስረታቸውን ገልጸዋል።

▪ በዩክሬን ዙሪያ ያለው ሁኔታ ከአላስካው የመሪዎች ጉባኤ የትኩረት ጉዳዮች አንዱ ነበር ሲሉ የሩሲያው መሪ ተናግረዋል።

▪ ሩሲያ የዩክሬንን ቀውስ ለማስቆም ፍላጎት እንዳላት እና በዩክሬን ደህንነት ላይ ለመሥራት ዝግጁ ናት ብለዋል።

▪ ፑቲን ከትራምፕ ጋር የተደረሰው የጋራ መግባባት ለዩክሬን ሰላም መንገድ እንደሚጠርግ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

▪ ፕሬዝዳንቱ ኪዬቭ እና አውሮፓ ሁኔታውን በመፍታት ዙሪያ ያለውን ለውጥ እንደማያደናቅፉ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።

▪ በሩሲያ እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለው የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥ በትራምፕ ዘመን ጨምሯል፤ ሁለቱ ሀገራት ከቴክኖሎጂ እስከ አርክቲክ አካባቢ ድረስ ብዙ የሚያቀርቡት ነገር አለ ሲሉ ፑቲን ተናግረዋል።

▪ የሩሲያው ፕሬዝዳንት የአሜሪካው አቻቸው ላደረጉት ታማኝ ንግግር አመስግነዋል።

▪ ፕሬዝዳንቱ በወቅቱ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቢሆኑ ኖሮ በዩክሬን ጦርነት እንደማይከሰት ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0