ትራምፕ ለሩሲያ ልዑካን ያደረጉት ደማቅ አቀባበል ለንግግር ከፍተኛ ተስፋን የሰነቀ ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱትራምፕ ለሩሲያ ልዑካን ያደረጉት ደማቅ አቀባበል ለንግግር ከፍተኛ ተስፋን የሰነቀ ነው
ትራምፕ ለሩሲያ ልዑካን ያደረጉት ደማቅ አቀባበል ለንግግር ከፍተኛ ተስፋን የሰነቀ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.08.2025
ሰብስክራይብ

ትራምፕ ለሩሲያ ልዑካን ያደረጉት ደማቅ አቀባበል ለንግግር ከፍተኛ ተስፋን የሰነቀ ነው

የዘመናዊ ሀገራት ዓለም አቀፍ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማርቲኖቭ እንደተናገሩት፤ በአላስካ ለሩሲያ ልዑካን የተደረገው አቀባበል ቅርፀት እና ፕሮቶኮል ትራምፕ ለሩሲያ እንግዶቻቸው ያላቸውን ልዩ ግምት አጉልቶ ያሳያል።

"ትራምፕ ልምድ ያላቸው ነጋዴ ከመሆናቸው አኳያ እንዴት ማስደመም እንዳለባቸው ያውቃሉ፤ ለሩሲያ ልዑካን የተሰጠው ትኩረት ጎልቶ ይታያል። ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ፕሬዝዳንቱ ለየትኛውም የፖለቲካ እንግዳ እንደዚህ አይነት መስተንግዶ አላደረጉም። ይህ ግልጽ መልዕክት ያስተላልፋል፤ ቀዳሚ እንግዶች እንደሆኑ እና በንግግሩ ትልቅ ተስፋ እንዳላቸው" ሲሉ ማርቲኖቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

በ1973 በሊዮኒድ ብሬዥኔቭ እና በሪቻርድ ኒክሰን መካከል ከተደረገው ስብሰባ ጋር ታሪካዊ ተመሳሳይነት እንዳለው በማንሳት፤ በጥንቃቄ በተዘጋጀ ዝርዝር ሁኔታ የተደረገው ደማቅ አቀባበል “ነገሮች ወደነበሩበት ሁኔታ ሊመለሱ እንደሚችሉ የሚጠቁም" መሆኑን አመላክተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0