የፑቲን እና የትራምፕ ስብሰባ ዛሬ ነሐሴ 9 ምሽት አራት ሠዓት ገደማ ይጀምራል፡፡ ስለ ስብሰባው የታወቁ ጉዳዮች፦

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየፑቲን እና የትራምፕ ስብሰባ ዛሬ ነሐሴ 9 ምሽት አራት ሠዓት ገደማ ይጀምራል፡፡ ስለ ስብሰባው የታወቁ ጉዳዮች፦
የፑቲን እና የትራምፕ ስብሰባ ዛሬ ነሐሴ 9 ምሽት አራት ሠዓት ገደማ ይጀምራል፡፡ ስለ ስብሰባው የታወቁ ጉዳዮች፦ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.08.2025
ሰብስክራይብ

የፑቲን እና የትራምፕ ስብሰባ ዛሬ ነሐሴ 9 ምሽት አራት ሠዓት ገደማ ይጀምራል፡፡ ስለ ስብሰባው የታወቁ ጉዳዮች፦

ስብሰባው የት ይካሄዳል?

በሰሜን ምዕራብ የአሜሪካ ግዛት አላስካ ኤልሜንዶርፍ ሪቻርድሰን የጦር ሰፈር ይደረጋል፡፡ አላስካ በአንድ ወቅት የሩሲያ ነበረች፡፡ በጦር ሰፈሩ አቅራቢያ ዘጠኝ የሶቪዬት ሕብረት አብራሪዎች እንዲሁም ከ1942 እስከ 1945 ከአሜሪካ አውሮፕላኖችን ሲያጓጉዙ የሞቱ የአራት ሰዎች መታሰቢያ መቃብር ይገኛል፡፡

ስብሰባው መቼ ይጀምራል?

ከምሽቱ አራት ሠዓት አካባቢ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ሁነቱ መሪዎቹ በአስተርጓሚዎች አማካኝነት የገጽ ለገጽ ውይይት ካካሄዱ በኋላ የሁለቱ ሀገራት ለዑካን ቡድኖች የ5 በ 5 ቅርጽ ድርድር ያካሂዳሉ፡፡ ስብሰባውን ተከትሎ የሩሲያ እና የአሜሪካ መሪዎች የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ፡፡

በሩሲያ ልዑክ ውስጥ እነማን ተካትተዋል?

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጊ ላቭሮቭ፣

የፕሬዝዳንታዊ አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ፣

የገንዘብ ሚኒስትር አንቶን ሲሏኖቭ፣

የመከለከያ ሚኒስትር አንድሪ ቦሉሶቭ፣

የሩሲያ ፌደሪሽን ፕሬዝዳንት የውጭ ሀገር ትብብር ልዩ ተወካይ እና የሩሲያ የቀጥታ ኢንቨስትመንት ፈንድ ኃላፊ ኪሪል ዲሚትሪቭ ናቸው፡፡

በምን ጉዳይ ላይ ይመከራል?

ዋናው ረዕሰ ጉዳይ የሩሲያ ግጭት እልባት ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ሁለቱ ወገኖች በአሳሳቢ ዓለም አቀፋዊና እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ፡፡ በተለይም የሩሲያው መሪ በሞስኮ እና በዋሽንግተን መካከል የጦር መሣሪያ ቁጥጥርን በተመለከተ አዳዲስ ስምምነቶች እንዲደረጉ ይሁንታቸውን ችረዋል፡፡

ዘለንስኪ ስብሰባው ላይ ይገኛሉ?

አይገኙም፡፡ ትራምፕ ከፑቲን ጋር ከሚያደርጉት ስብሰባ በኋላ ከዘለንስኪ ጋር ሁለተኛ ስብሰባ ለማዘጋጀት እንደሚደውሉላቸው ተናግረዋል፡፡ ፑቲን ከዘለንስኪ ጋር ስብሰባ ማካሄድ የሚቻል መሆኑን ገልፀው እስካሁን ያለተሟሉ የድርድር ቅድመ ሁኔታዎች መቀመጥ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

ስብሰባውን ተከትሎ የሚፈረም ሰነድ ይኖራል?

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ፣ ስብሰባውን ተከተሎ ሰነድ የመፈራረም ዕቅድ የለም ብለዋል፡፡ እንደ እሳቸው ፑቲን እና ትራምፕ ማሳካት የሚችሏቸውን ስምምነቶች መጠን እና ግንዛቤዎች ዝርዝር የሚገልፁ ይሆናል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0