አውሮፓውያን የሰላም ሂደቱን ለማስተጓጎል ጥረት የሚያደርጉት ሩሲያን አሸናፊ ሰለሚያደረግ ነው - ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት
11:15 15.08.2025 (የተሻሻለ: 11:24 15.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአውሮፓውያን የሰላም ሂደቱን ለማስተጓጎል ጥረት የሚያደርጉት ሩሲያን አሸናፊ ሰለሚያደረግ ነው - ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አውሮፓውያን የሰላም ሂደቱን ለማስተጓጎል ጥረት የሚያደርጉት ሩሲያን አሸናፊ ሰለሚያደረግ ነው - ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት
ዩክሬን የትራምፕ እና ፑቲንን ውይይት ለማደናቀፍ ያቀደችውን የተቀነባበረ የሀሰት ዘመቻ አስመልክቶ ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየታቸውን የሰጡት የቀድሞው አምባሳደር ጥሩነህ ዜና፤ የዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ኪዬቭን በጄ ሊላት ይገባል ብለዋል፡፡
“ትራምፕ ለዚህ አላስፈላጊ ጦርነት መፍትሄ ለማምጣት እየሞከሩ ነው፡፡ ነገር ግን ዩክሬናውያኑ ይህን የሰላም ሂደት ለመቀልበስ በሚያደርጉት ጥቃት ራሳቸውም አይጠቀሙም፣ ለሰላም ሂደቱም ጥሩ አይሆንም እንዲሁም በአካባቢው ሰላም ለማምጣት ጥረት እያደርጉ ያሉትን ትራምፕ አይጠቅምም” ሲሉ ሃሳባቸውን ገልፀዋል፡፡
ባለሙያው የዩክሬን ስፖንሰሮች አውሮፓውያኑ የሰላም ጥረቶችን የሚያስተጓጉሉበትን ምክንያትም አብራርተዋል፦
◻ አውሮፓውያን ሩሲያ ተሸንፋ ማየት ስለሚፈልጉ ደስተኞች አይደሉም፣
◻ ጦርነቱ ለረጅም ግዜ እንዲቆይ እና ሩሲያ እንድትዳከም ይፈልጋሉ፣
◻ ማንም ማየት እንደሚችለው ግን፤ ያ በጭራሽ አይሆንም፡፡
ዲፕሎማቱ አክለውም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጦርነቱ የሚቀጥል ከሆነ ሩሲያ እንደማትቻል ተረድተዋል ያሉ ሲሆን፤ ከተሳሳተ ጎን ቆመዋል ባሏቸው አውሮፓውያን እና ዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለው ግንኙነት ስብራት እንደገጠመውም አንስተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X