ሉሲ እና ሰላም ወደ ማዕከላዊ አውሮፖዊቷ ሀገር ቼክ ሪፐብሊክ ተጓዙ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሉሲ እና ሰላም ወደ ማዕከላዊ አውሮፖዊቷ ሀገር ቼክ ሪፐብሊክ ተጓዙ
ሉሲ እና ሰላም ወደ ማዕከላዊ አውሮፖዊቷ ሀገር ቼክ ሪፐብሊክ ተጓዙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.08.2025
ሰብስክራይብ

ሉሲ እና ሰላም ወደ ማዕከላዊ አውሮፖዊቷ ሀገር ቼክ ሪፐብሊክ ተጓዙ

የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ በቦሌ ኤርፖርት በመገኘት ለሉሲ እና ሰላም ሽኝት ማድረጋቸውን ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሉሲ (ድንቅነሽ) እና ሰላም ቅሪተ አካሎች ፕራግ በሚገኘው ብሔራዊ ሙዚዬም ከነሐሴ 19 ቀን 2017 ጀምሮ ለ60 ቀናት ለዕይታ ይቀርባሉ::

የቱሪዝም ሚኒስትሯ "ዐውደ ርዕዩ የኢትዮጵያን ምድረ ቀደምትነት ለዓለም ማረጋገጫ ነው፡፡ እስከዛሬ ኢትዮጵያ ሉሲን አስተዋውቃለች አሁን ደሞ ሉሲ አዲሲቷን ኢትዮጵያን ለዓለም ታስተዋውቃለች" ብለዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ |

አዳዲስ ዜናዎች
0