ናይጄሪያ በአፍሪካ ቀዳሚ የነዳጅ አምራችነቷን አስጠበቀች
19:52 14.08.2025 (የተሻሻለ: 19:54 14.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ናይጄሪያ በአፍሪካ ቀዳሚ የነዳጅ አምራችነቷን አስጠበቀች
የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር የድፍድፍ ነዳጅ ምርት መጠነኛ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ይህም በዓመት ውስጥ የነዳጅ አምራችና ላኪዎች ሀገራት ማኅበር (ኦፔክ) በአንድ ቀን 1.5 ሚሊየን በርሜል የማምረት ኮታን ለሦስተኛ ጊዜ የተሻገረ መሆኑን ኦፔክ በነሐሴ ወር ሪፖርቱ አስታውቋል፡፡
በናይጄሪያ ሪፖርት የተደረገው የ1.507 ሚሊየን በርሜል ዕለታዊ ምርት ሰኔ ላይ ከነበረው በቀን 2 ሺህ በርሜል ከፍ ያለ ነው፡፡
የኦፔክ መረጃ ደግሞ በቀን 1.559 ሚሊየን በርሜል በመተንበይ የ16 ሺህ በርሜል ዕለታዊ ጭማሪ መኖሩን ያሳያል፡፡
ከዚህ ቀደም በስርቆት እና በማስተላለፊያ ቧንቧ ዝርጋታ ላይ በደረሰ ውድመት ምክንያት የምርት ኮታዋን ለመሙላት ስትቸገር ብትቆይም፤ የናይጄሪያ ብሔራዊ የነዳጅ ኮርፖሬሽን የ2024 የአስቸኳይ ጊዜ ምርት አዋጅ እና በማፋሰሻ ጣቢያ መለኪያ ላይ የተደረገውን የ21 ሚሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ጨምሮ በቅርቡ የተወሰዱ እርምጃዎች ውጤት እያመጡ ነው፡፡
ኦፔክ ናይጄሪያ ገቢ ለመጨመር እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማሳደግ በማለም በ2026 ተግባራዊ ለምታደርጋቸው የግብር ሪፎርሞች እውቅና ሰጥቷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X