#viral| ‘ይህን የምንሠራው ለማርያም ነው’፤ የጣልያን የባሕር ዳርቻ ቤተ ክርስቲያን እውቅ ጉልላትን የሚያድሱ ‘ጠባቂ መላዕክት’ን ይተዋወቁ
19:43 14.08.2025 (የተሻሻለ: 19:44 14.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
#viral| ‘ይህን የምንሠራው ለማርያም ነው’፤ የጣልያን የባሕር ዳርቻ ቤተ ክርስቲያን እውቅ ጉልላትን የሚያድሱ ‘ጠባቂ መላዕክት’ን ይተዋወቁ
በፖዚታኖ ጎህ ሲቀድና የአማልፊ የባሕር ዳርቻ በስስ ወርቃማ ብርሃን ሲሸፈን፣ ሁለት ሰዎች ወደ ሰማይ ከፍ ይላሉ፡፡ በእርግጥ ክንፍ ኖሯቸው ሳይሆን በገመድ እና በወገባቸው በሚያገለድሟቸው ኮርቻዎች ነው፡፡
የከተማዋ ዋና ቤተ ክርስቲያን "የጠባቂ መላእክት" በመባል የሚታወቁት በጎ ፈቃደኞች ፋቢዮ ፉስኮ እና አንቶኒኖ ዴ ሲሞን፣ በየዓመቱ የቤተ ክርስቲያኑን ታዋቂ የማጆሊካ ሸክላ ንጣፍ ጉልላት "የማስዋብ እድሳት" ያደርጋሉ፡፡
በሕንፃው ምሉዕ ሞዛይክ ከሚፈጥሩት ፀሐያማ ቢጫ፣ አረንጓዴ እና ሰማያዊ ንጣፎች ሥራቸውን ጀምረው፤ በንጣፎቹ መካከል የበቀሉትን የበጋ አረሞችን በጥንቃቄ ያስወግዳሉ፡፡
"ይህን የምናደርገው እኛን ስለምትጠብቀን ማርያም ብለን ነው" የሚሉት ጎህ ከመቅደዱ በፊት ነቅተው የተነሱ ቱሪስቶች በጉጉት ፎቶ የሚያነሷቸው በጎ ፈቃደኞቹ ናቸው። "ፀሐይ ስትወጣ ከጉልላቱ አናት ላይ የሚፈጠረው አስደናቂ ዕይታ የጥረታችን ምርጡ ሽልማት ነው።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X