አውሮፓውያን እና ዩክሬን የፑቲን እና የትራምፕ ስብሰባ “እንዳይካሄድ የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት አድርገዋል” - ፕሮፌሰር አየለ በክሪ
19:13 14.08.2025 (የተሻሻለ: 19:14 14.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአውሮፓውያን እና ዩክሬን የፑቲን እና የትራምፕ ስብሰባ “እንዳይካሄድ የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት አድርገዋል” - ፕሮፌሰር አየለ በክሪ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አውሮፓውያን እና ዩክሬን የፑቲን እና የትራምፕ ስብሰባ “እንዳይካሄድ የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት አድርገዋል” - ፕሮፌሰር አየለ በክሪ
ዩክሬን እንደ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ ያሉ አብዛኞቹ የአውሮፓ ሀገራት አብረዋት እንዲቆሙ አጥብቃ ዘመቻ ማድረጓን የገለፁት የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኙ፤ “አብዛኞቹ የአውሮፓ ሀገራት ዩክሬን ሩሲያን እንድታሸንፍ በየትኛውም መንገድ ሊያስታጥቋት አይችሉም፡፡ አቅም የላቸውም፣ ሀብት የላቸውም፣ በመካከላቸውም አንድነት የላቸውም” ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል፡፡
የዓለም አቀፍ ጉዳይ ተንታኙ ያነሷቸው ተጨማሪ ነጥቦች፦
ዩክሬን ሩሲያውያንን ለማሸነፍ በምንም አይነት ቁመና ላይ አይደለችም፣
ብሪክስ ወሳኝ የኃይል ምንጭ እየሆነ መጥቷል፣
አዲሱ የሥርዓተ ዓለም ባለብዙ ወገን ነው፣
አዲሱ ሥርዓተ ዓለም ሊቀለበስ ወደማይችልበት ቁመና እየተሸጋገረ ነው፡፡
የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር አየለ፤ ፑቲን ለአላስካ ስብሰባ ይሁንታቸውን የመሰጠታቸው ውሳኔ አንድምታን በተመለከተ ሲናገሩ፤ ከአሜሪካ ጋር መደበኛ፣ አዎንታዊ እና መልካም ግንኙነት እንዲኖራቸው ያላቸውን መሻት ያሳዩበት እንደሆነ አመላክተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X