አፍሪካውያን ዓለም አቀፍ የክፍያ ሥርዓቶችን መጠቅም በመተው በራሳቸው የቴክኖሎጂ አማራጮች መገልገል እንዳለባቸው የሳይበር ደኅንነት ባለሙያው ተናገሩ

ሰብስክራይብ

አፍሪካውያን ዓለም አቀፍ የክፍያ ሥርዓቶችን መጠቅም በመተው በራሳቸው የቴክኖሎጂ አማራጮች መገልገል እንዳለባቸው የሳይበር ደኅንነት ባለሙያው ተናገሩ

በአፍሪካ አሕጉራዊ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች ይበልጥ ማስፋፋት እንደሚገባ ባለሙያው አቶ ብሥራት ይርዳው ጠቁመዋል።

"በሌሎች የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ ጥገኛ መሆን የለብንም። በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል ወይም በኢትዮጵያ አና በደቡብ አፍሪካ መካከል የሚደረግ ግብይትም የግድ በዓለም አቀፍ የክፍያ አማራጮች በኩል ማለፍ የለበትም። እኛ የራሳችን የፓን አፍሪካ የክፍያ ስርዓት አለን። እሱን መጠቀም እንችላለን" ብለዋል።

ባለሙያው ገንዘብ ለማስተላለፍ የሚወጣን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማዳን እና በነጻነት መገበያየት ለሚያስችሉ አፍሪካዊ የዘርፉ ፈጠራዎች ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባም፤ 23ኛው ዙር የተቀናጀ የኢትዮጵያ የባንክ ሥርዓት፤ የፈጠራ እና የላቀ ሽልማት መድረክ ላይ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ አስታውቀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0