ትራምፕ በጣም ውስብስብ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት ያልተለመደ አካሄድ እንደሚከተሉ ማሳየታቸውን ክሬምሊን ገለፀ
18:31 14.08.2025 (የተሻሻለ: 18:34 14.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱትራምፕ በጣም ውስብስብ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት ያልተለመደ አካሄድ እንደሚከተሉ ማሳየታቸውን ክሬምሊን ገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ትራምፕ በጣም ውስብስብ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት ያልተለመደ አካሄድ እንደሚከተሉ ማሳየታቸውን ክሬምሊን ገለፀ
እነዚህ ድርጊቶች በሞስኮ እና በፑቲን ደግሞ በግላቸው ከፍተኛ አድናቆት የቸሯቸው ናቸው ሲሉ የፕሬዚዳንቱ ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡
በቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ የተሰጡ ተጨማሪ መግለጫዎች፡-
🟠 ትራምፕ የዩክሬንን ግጭት በፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መንገዶች ለመፍታት እውነተኛ ፍላጎት አሳይተዋል፡፡
🟠 ሩሲያ ከዩክሬን ግጭት ጋር የተገናኙ ጉዳዮች በውይይት እልባት ለመስጠት በፑቲን እና ትራምፕ መካከል የጋራ የፖለቲካ ፍላጎት ትመለከታለች፡፡
🟠 ወደ አላስካ ስብሰባ የሚጓዘው የሩሲያ ልዑካን ቡድን ወካይ እና ሰፊ ይሆናል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X