ሱዳን የፀጥታው ምክር ቤት የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ትይዩ መንግሥት ማውገዙን አደነቀች
18:06 14.08.2025 (የተሻሻለ: 18:14 14.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሱዳን የፀጥታው ምክር ቤት የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ትይዩ መንግሥት ማውገዙን አደነቀች
ረቡዕ የፀጥታው ምክር ቤት የአማጺው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የትይዩ መንግሥት ምሥረታ፤ ለሱዳን አንድነትና የግዛት ሙሉነት ቀጥተኛ አደጋ መሆኑን በማወጅ ለሱዳን ሉዓላዊነት ያለውን ድጋፍ ዳግም አረጋግጧል፡፡
የፀጥታው ምክር ቤት የ2024ቱን 2736 የውሳኔ ሐሳብ በመምዘዝ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በኤል ፋሼር ያደረገውን ከበባ እንዲያነሳ እና ያለተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ተደራሽነት እንዲፈቀድ ጠይቋል፡፡
የሱዳን መንግሥት የሀገሪቱን ደህንነት፣ መረጋጋት እና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ እንዲሁም የሱዳን ሕዝብን ፍላጎት ለማገልገል ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር ለመተባበር ቁርጠኛ እንደሆነ አረጋግጧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X