ኢትዮጵያ በሱዳን በኩል ከግብፅ ጋር የኃይል ትስስር የመፍጠር ፍላጎት እንዳላት ገለፀች

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በሱዳን በኩል ከግብፅ ጋር የኃይል ትስስር የመፍጠር ፍላጎት እንዳላት ገለፀች

የኢትዮጵያ የኃይል ሽያጭ ከውጭ ምንዛሬ ግኝት ባለፈ አፍሪካን በኃይል የማስተሳሰር ራዕይ የሰነቀ እንደሆነ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴዔታ ኢ/ር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"ኢትዮጵያ በሁሉም ክልል የኤሌክትሪክ ኃይልን በማዳረስ ረገድ ቁልፍ ሚና እየተጫወተች ነው። ራዕያችን በጣም ትልቅ ነው። እኛ ቀደም ብለን ወደ ጎረቤት ሀገራት ኃይል በመላክ ላይ እንገኛለን” ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታው አክለዋል፡፡

“በቀጣይም የምስራቅ አፍሪካን የኃይል መስመር ከደቡብ አፍሪካ ጋር ለማገናኘት እንሠራለን" ሲሉ የፋይናንስ አካታችነትን በማስቻል ማኀበረሰቡን የጸሐይ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ ላይ አተኩሮ በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ገልጸዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0