የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣሕለወርቅ ዘውዴ የኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክን የሰላም ሂደት እንዲያስተባብሩ ተመረጡ
15:55 14.08.2025 (የተሻሻለ: 16:04 14.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣሕለወርቅ ዘውዴ የኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክን የሰላም ሂደት እንዲያስተባብሩ ተመረጡ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣሕለወርቅ ዘውዴ የኮንጎ ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክን የሰላም ሂደት እንዲያስተባብሩ ተመረጡ
የዚምባብዌ መሪ የምሥራቅ ኮንጎ ግጭት ዋና መንሳኤ በጄ እንዲባል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የደቡብ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ ሊቀመንበር ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ፤ ከምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ሊቀመንበር የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር በመሩት የቨርቹዋል ጉባኤ ላይ ነው ጥሪውን ያቀረቡት፡፡
“ክቡራን፤ እህት ሀገር ኮንጎ ዴሞክራሲያው ሪፐብሊክ ያጋጠሟትን ፈተናዎች ለመፍታት በጋራ ባለን ቁርጠኝነት ላይ ለመሳተፍ ጊዜ ስለሰጣችሁን አመሰግናለሁ” ሲሉ ምናንጋግዋ ለአፍሪካ መሪዎች ተናግረዋል፡፡
ጉባኤው አምስት የቀድሞ የአፍሪካ ፕሬዝዳንቶችን በአስተባባሪነት በይፋ ሾሟል፡፡
ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ (ናይጄሪያ)
ኡሁሩ ኬንያታ (ኬንያ)
ካትሪኔ ሳምባ-ፓንዛ (ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ)
ሣሕለወርቅ ዘውዴ (ኢትዮጵያ)
ሞክግዌትሲ ማሲሲ (ቦትዋና)
ምናንጋግዋ እና ሩቶ፤ የደቡብ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ (የሉዋንዳ) እና የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ (የኬንያ) የተናጠል የሰላም ሂደቶች ወደ አንድ አፍሪካ መር ተነሳሽነት እንዲዋሃዱ ወስነዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X