የመን ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ ዘመቻ መጀመሯን አስታወቀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየመን ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ ዘመቻ መጀመሯን አስታወቀች
የመን ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ ዘመቻ መጀመሯን አስታወቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.08.2025
ሰብስክራይብ

የመን ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ ዘመቻ መጀመሯን አስታወቀች

የየመን ባለሥልጣናት በደቡብ አብያን ግዛት ጀልባ ሰጥሞ ከ90 በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መሞታቸውን ተከትሎ፤ አፍሪካውያን ስደተኞችን በሀገሪቱ በኩል የሚያንቀሳቅሱ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ ዘመቻ መጀመራቸውን ረቡዕ አስታውዋል፡፡

የአብያን ግዛት ፖሊስ ባወጣው መግለጫ፤ "የአፍሪካ ዜግነት ያላቸውን ፍልሰተኞች እና ስደተኞችን በማጓጓዝ ወይም በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ተሳትፎ የተገኘ የተኛውም አካል ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ" ገልጿል፡፡

በአዲሱ እርምጃ መሠረት፤ የፀጥታ ኃይሎች በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር አግልግሎት ላይ የሚውሉ ተሽከርካሪዎችን፣ ጀልባዎችን እና ሌሎች የመጓጓዣ ዘዴዎችን የሚወርሱ ይሆናል፡፡

በአቢያን የባሕር ዳርቻ ላይ በደረሰው የጀልባ አደጋ 92 ሰዎች መሞታቸው የተረጋገጠ ሲሆን ሌሎች አሁንም የገቡበት አልታወቀም፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0