የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የዓለም አቀፍ የፀሐይ ኃይል ጥምረት በፀሐይ ኃይል ቴክኖሎጂ የሶላር ሚኒግሪድና የሶላር ፓርክ ፕሮጀክት ግንባታ ለማስጀመር ስምምነት ተፈራረሙ
12:21 14.08.2025 (የተሻሻለ: 12:34 14.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የዓለም አቀፍ የፀሐይ ኃይል ጥምረት በፀሐይ ኃይል ቴክኖሎጂ የሶላር ሚኒግሪድና የሶላር ፓርክ ፕሮጀክት ግንባታ ለማስጀመር ስምምነት ተፈራረሙ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የዓለም አቀፍ የፀሐይ ኃይል ጥምረት በፀሐይ ኃይል ቴክኖሎጂ የሶላር ሚኒግሪድና የሶላር ፓርክ ፕሮጀክት ግንባታ ለማስጀመር ስምምነት ተፈራረሙ
ስምምነቱ የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት፣ የኢነርጂ ተደራሽነትን ለማጎልበት እና ፈጠራ እና ዘላቂ የኃይል አማራጮችን በመጠቀም ኢኮኖሚን ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡
የስምምነቱ ዋና ዋና ይዘቶች፦
የ400 ሜጋ ዋት ሶላር ፓርክ ግንባታ፣
700 ኪሎዋት ሰዓት ሶላር ሚኒ ግሪድ ማስጀመር፣
የመስኖ እና መጠጥ ውሃ አቅርቦት ማሳደግ፣
የፋይናንስና የቴክኖሎጂ ትብብር ዕድሎችን መፍጠር ናቸው፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ “ኢትዮጵያ የፀሐይ ኃይልን ጨምሮ እምቅ የኃይል አማራጮችን ጥቅም ላይ ለማዋል በትኩረት እየሠራች ነው” ብለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X