የኢትዮጵያ ግድብ ጉዳት የሚፈጥር ከሆነ ግብጽ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት እርምጃ ትወስዳለች - የግብጽ ከፍተኛ ዲፕሎማት
10:49 14.08.2025 (የተሻሻለ: 10:54 14.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ግድብ ጉዳት የሚፈጥር ከሆነ ግብጽ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት እርምጃ ትወስዳለች - የግብጽ ከፍተኛ ዲፕሎማት

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ግድብ ጉዳት የሚፈጥር ከሆነ ግብጽ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት እርምጃ ትወስዳለች - የግብጽ ከፍተኛ ዲፕሎማት
በታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ላይ የሚደረጉ ድርድሮች ቆመዋል፤ ግድቡ የሀገሪቱን የውሃ ፍላጎት የሚነካ ከሆነ ግብጽ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት እርምጃ እንደምትወስድ፤ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በድር አብዴላቲ ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ ኤል-ሲሲ ግብጽ በውሃ ደህንነቷ ላይ ስጋት ሲፈጠር ባላየ እንደማታልፍ፣ ናይል ወንዝን በተመለከተ ተናጠላዊ እርምጃዎችን እንደማትቀበል እና የውሃ ጉዳይ ግብጽ ላይ ተጽዕኖ የመፍጠር ዘመቻ አካል ነው ሲሉ ማክሰኞ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ “የግብጽ አቋም ግልጽ ነው፡፡ በግድቡ ዙሪያ የሚደረገው ድርድር ቆሟል፡፡ ሁኔታውን እየተከታተልን ነው፤ ማናቸውንም ተናጠላዊ እርምጃዎች እንቃወማለን፡፡ ጉዳት ከደረሰብን በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት የውሃ ፍላጎታችንን ለመከላከል እርምጃዎችን ለመውሰድ እንገደዳለን” ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን እና በመጪው መስከረም ወር እንደሚመረቅ ሰኔ መጨረሻ አስታውቀዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X