በሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የተገለጠው የትንኮሳ እቅድ ኪዬቭ ዘመኑን፣ አቅሟን እና ስለተጋጣሚዋ መሳሳቷን ያሳያል ሲሉ የፖለቲካ ተንታኙ ተናገሩ
10:31 14.08.2025 (የተሻሻለ: 10:34 14.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የተገለጠው የትንኮሳ እቅድ ኪዬቭ ዘመኑን፣ አቅሟን እና ስለተጋጣሚዋ መሳሳቷን ያሳያል ሲሉ የፖለቲካ ተንታኙ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የተገለጠው የትንኮሳ እቅድ ኪዬቭ ዘመኑን፣ አቅሟን እና ስለተጋጣሚዋ መሳሳቷን ያሳያል ሲሉ የፖለቲካ ተንታኙ ተናገሩ
“በመሠረቱ የሩሲያ ደህንነት የዚህ ሴራ መረጃ አስቀድሞ ማግኘቱ የትንኮሳውን አደጋ ለመተንበይ ብቻ ሳይሆን፤ ከሁሉም ይልቅ ኪዬቭ በራሷ ሕዝብ ላይ የምታደርሰውን የሽብር ፍጅት መላው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲታዘብ የሚያስችል ነው” ሲሉ ሊያንሁዌ ኢምሆቴፕ ባያላ ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡
የፑቲን እና የትራምፕ ስብሰባ “በመጨረሻም መደረጉ እውን ነው፤ በአሜሪካ እና በሩሲያ መካከል የሰላም ስምምነት ተፈጥሮ ነገሮች መስመር ሊይዙ ይችላሉ” በማለት ለሰላም ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡
እናም “በቀጣናው የሰላም ጠንቅ የሆነችው” ኪዬቭን የሚያሳስባትም ይኸው ነው፡፡
ዩክሬን "የሰላም ሂደቱን ለመተው፣ የሰላም ሂደቱን ለማዘግየት መረጃዎችን በመሰብሰብ እና ክርክሮችን በማደራጀት ላይ ተሰማርታለች" ሲሉ ተንታኙ አክለዋል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X