ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ አመራር ሁሉም ውሳኔዎች የማይናወጥ ድጋፍ እንደምትሰጥ ኪም ጆንግ ኡን ለፑቲን ገለፁ
18:09 13.08.2025 (የተሻሻለ: 18:14 13.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ አመራር ሁሉም ውሳኔዎች የማይናወጥ ድጋፍ እንደምትሰጥ ኪም ጆንግ ኡን ለፑቲን ገለፁ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ አመራር ሁሉም ውሳኔዎች የማይናወጥ ድጋፍ እንደምትሰጥ ኪም ጆንግ ኡን ለፑቲን ገለፁ
የኮሪያ ዲሞክራሲያዊ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ “በሪፑብሊኳ እና በሩሲያ መካከል ለተፈረመው ውል ታማኝ ሆና ትቀጥላለች” ሲሉ ኪም ጆን ኦን ለሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ማረጋገጣቸውን የኮሪያ ማዕከላዊ የዜና ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡
ኪም ጆንግ ኡን፤ ቭላድሚር ፑቲን የኮሪያ ነጻነት 80ኛ ዓመት በዓልን አስመልክቶ ሞቅ ያለ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ለሰሜን ኮሪያ ሕዝቦች በማድረሳቸው ልባዊ ምሥጋናቸውን ገልጸዋል።
ፑቲን እና ኪም የስልክ ውይይት ተጨማሪ ነጥቦች፦
የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በጋራ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ ምልከታቸውን ተለዋውጠዋል፡፡
ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማሳደግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም አረጋግጠዋል፡፡
በሁሉም ዘርፎች የትብብር ግንኙነታቸው እየጠነከረ መምጣቱን አድንቀዋል፡፡
አርብ ነሐሴ 15 የኮሪያ ሕዝቦች ነጻነት 80ኛ ዓመት ሲከበር፤ ለኮሪያ ነጻነት ሕይወታቸውን የሰጡ የሶቪዬት ወታደሮች ይዘከራሉ፡፡
የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በሁሉም ዘርፎች የትብብር ግንኙነታቸው እየጠነከረ መምጣቱን አድንቀው፤ ወደፊትም ትብብራቸውን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X