ደቡብ አፍሪካ የአሜሪካን የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት 'በስህተት የታጨቀ' ነው ስትል ተቃወመች
16:15 13.08.2025 (የተሻሻለ: 17:14 13.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱደቡብ አፍሪካ የአሜሪካን የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት 'በስህተት የታጨቀ' ነው ስትል ተቃወመች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ደቡብ አፍሪካ የአሜሪካን የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርት 'በስህተት የታጨቀ' ነው ስትል ተቃወመች
ማክሰኞ ዓመታዊ የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርቱን ይፋ ያደረገው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካነሮችን (ነጭ ደቡብ አፍሪካውያንን) መሬት ለመንጠቅ እና በዘር ሕዳጣኖች ላይ ተጨማሪ በደል ለማደረስ “በጣም አሳሳቢ እርምጃ ወስዳለች" ሲል ከስሷል፡፡
ደቡብ አፍሪካ በአብዛኞቹ የወጪ ንግድ ምርቶቿ ላይ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ ነው የተባለው የ30 በመቶ ቀረጥ በአሜሪካ ከተጣለባት በኋላ የመጣ ሪፖርት ነው፡፡ የትራምፕ አስተዳደር የዘር የመብት ልዩነቶችን ለማስተካከል ያለሙ የመሬት እና የሥራ ፈጠራ ፖሊሲዎችን በመተቸት እርምጃውን እንደወሰደ መግለጹ የሚታወስ ነው፡፡
የፕሪቶሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሪፖርቱ "በከፍተኛ እንዳዘነ" በመግለፅ፤ የደቡብ አፍሪካን ሕገ-መንግሥታዊ ዴሞክራሲ እውነታ አሳስቶ የሚያቀርብ ብሎታል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X