በመጪው የፑቲን እና ትራምፕ ስብሰባ ዙሪያ የሚሰጡ ምላሾች ‘ማን ከየተኛው ወገን’ እንደሆነ ያሳያ ነው ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስተያየታቸውን አጋርተዋል
15:26 13.08.2025 (የተሻሻለ: 17:14 13.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በመጪው የፑቲን እና ትራምፕ ስብሰባ ዙሪያ የሚሰጡ ምላሾች ‘ማን ከየተኛው ወገን’ እንደሆነ ያሳያ ነው ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስተያየታቸውን አጋርተዋል
ዓለም ከነሐሴ 9 የአላስካ ስብሰባ መፍትሄ በሚጠብቁ ባለተስፋዎች እንዲሁም "በቁጣ በሚያፏጩ እና ሂደቱን ለማደናቀፍ በሚያሴሩ" መካከል መከፈሉን ማሪያ ዛካሮቫ ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንደሚሉት፤ የፑቲን እና የትራምፕ ስብሰባ ላይ የሚሰጡት አስተያየቶች ሁሉ፤ የአስተያየት ሰጪዎቹን አቋም ማንፀባረቂያ ናቸው፡፡
በተለይ እየተንገበገቡ ያሉ ተቺዎች ሰለ ጉዳዩ ሳይሆን ስለተገፉ "እኛስ? ወንበር አምጡልን፣ ጠረጴዛውን አስፉት፣ መስኮቶቹን ክፈቱልን፣ እንወጣለን፣ እንበርራለን፣ እንፏቀቃልን፣ ታዩናላችሁ፣ ካስፈለገን በገመድ እንወርዳለን" እያሉ ይጮኻሉ ሲሉ አክለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X