ኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዋን ከውጭ ጥሬ ዕቃዎች ጥገኝነት ለመቀነስ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን ለማሳደግ የ25 ዓመት እቅድ አስጀመረች
14:13 13.08.2025 (የተሻሻለ: 14:14 13.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዋን ከውጭ ጥሬ ዕቃዎች ጥገኝነት ለመቀነስ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን ለማሳደግ የ25 ዓመት እቅድ አስጀመረች

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዋን ከውጭ ጥሬ ዕቃዎች ጥገኝነት ለመቀነስ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን ለማሳደግ የ25 ዓመት እቅድ አስጀመረች
ማክሰኞ ዕለት ይፋ የተደረገው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ኢኒሸቲቭ፤ ከ2025 እስከ 2050 የሚቆይ ሲሆን የመንግሥት የ2021-30 የልማት ማዕቀፍ አካል ነው፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ “ኢኒሼቲቩ ጥራትን መሠረት ያደረገ፣ ፈጠራን ያማከለ፣ ከሙስና የራቀ፣ አካታች እንዲሁም ሥልጣኔያችን እና ፀጋችንን ማሳየት የሚችል ዘርፍ ለመፈጠር አልሟል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ የኢኒሼቲቩን አራት ዋና ዋና ትኩረቶችንም አስቀምጠዋል፦
ቴክኖሎጂ መር አገልግሎትን ማላመድ፣
የላቀ አፈጻጸም ያላቸውን ባለሙያዎች እውቅና መስጠት፣
የመንግሥት እና የግል ዘርፍ አጋርነት ማጠናከር እና
ለዘርፉ አገልገሎት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት ናቸው፡፡
የኮንስትራክሽን ዘርፍ ከ10 በመቶ በላይ የሥራ ዕድል እና 20 በመቶ ገደማ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት እንደሚሸፍን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ |
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
