የኪዬቭ አገዛዝ የሩሲያ እና የአሜሪካ የመሪዎች ጉባኤን ለማደናቀፍ እንዳቀደ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ
21:08 12.08.2025 (የተሻሻለ: 21:44 12.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኪዬቭ አገዛዝ የሩሲያ እና የአሜሪካ የመሪዎች ጉባኤን ለማደናቀፍ እንዳቀደ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኪዬቭ አገዛዝ የሩሲያ እና የአሜሪካ የመሪዎች ጉባኤን ለማደናቀፍ እንዳቀደ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ
አርብ ከሚካሄደው የሩሲያ-አሜሪካ የመሪዎች ጉባኤ በፊት የዩክሬን ጦር ሰው በሚበዛባቸው ቹቪቭ አካባቢዎች ወይም ሆስፒታል ላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ሚሳኤሎችን በመጠቀም ቀስቃሽ ጥቃት ማቀዱን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ በኪዬቭ አገዛዝ ቁጥጥር ስር ባሉ ሌሎች አካባቢዎች ውስጥ የትንኮሳ ጥቃቶች ሊካሄዱ እንደሚችሉም ጠቁሟል።
ኪዬቭ የውጭ ጋዜጠኞችን በዩክሬን የደህንት አገልግሎት ትራንስፖርት ወደ ቹርጌቭ በማጓጓዘ "ሪፖርቶችን ለማቀነባበር" ዝግጅት ማድረጓንም የመከላከያ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በእቀዱ መሠረት በርካታ ሰላማዊ ዜጎች እንደሚገደሉ እና ይህ የዩክሬን ጦር የትንኮሳ ጥቃት በምዕራባውያን ጋዜጠኞች ወዲያውኑ "እንደሚመዘገብ" ነው የተመላከተው። ለኪዬቭ የትንኮሳ ጥቃት እና ለሲቪል ሰለባዎች ተጠያቂነቱን በሙሉ ሩሲያ ለመጣል መታቀዱንም የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X