ደቡብ አፍሪካ ከአሜሪካን ታሪፍ ራሷን ለመመከት የኢንዱስትሪ የጥበቃ እርምጃዎችን ልትወስድ ነው
20:54 12.08.2025 (የተሻሻለ: 21:04 12.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱደቡብ አፍሪካ ከአሜሪካን ታሪፍ ራሷን ለመመከት የኢንዱስትሪ የጥበቃ እርምጃዎችን ልትወስድ ነው

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ደቡብ አፍሪካ ከአሜሪካን ታሪፍ ራሷን ለመመከት የኢንዱስትሪ የጥበቃ እርምጃዎችን ልትወስድ ነው
የደቡብ አፍሪካ ንግድ ሚኒስትር ፓርክስ ታው፤ ሀገሪቱ የትራምፕ አስተዳደር በደቡብ አፍሪካ ምርቶች ላይ የጣለውን 30% ቀረጥ ለመመከት፤ በዝቅተኛ ዋጋ የሚገቡ ምርቶችን መገደብ እና ሌሎች የመከላከያ እርምጃዎችን ለመውሰድ ማቀዷን ገልፀዋል።
ደቡብ አፍሪካ ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ እና የንግድ ድርድሮች በመካሄድ ላይ በመሆናቸው በጃፓን፣ ቬትናም፣ ታይላንድ፣ ህንድ እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅ አዳዲስ ገበያዎችን በንቃት እየፈለገች ነው።
ፕሪቶሪያ በተጨማሪም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና አማካኝነት ክልላዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር አቅዳለች።
በሌላ በኩል ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን የሚያቀርቡ አካላትን ቅንጅትና የመረጃ ልውውጥ ለማሳለጥ በውድድር ሕግ ላይ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ታቅዷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X