ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በዓሣ ምርት በቀጣናው ሀገራት መካከል ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለመፍጠር እንደሚያግዝ ኢጋድ ገለጸ

ሰብስክራይብ

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በዓሣ ምርት በቀጣናው ሀገራት መካከል ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለመፍጠር እንደሚያግዝ ኢጋድ ገለጸ

"ግድቡ ይበልጥ ዓሳዎችን አምርቶ ወደ ጎረቤት አገራት መላክ ቢያስችል፤ ለኢኮኖሚያዊ ውህደት መሣሪያ ይሆናል። ኢትዮጵያውያንም የባሕር ዓሣ ቢፈልጉ ከጂቡቲ፣ ሶማሊያ እና ኬንያ ማስመጣት ይችላሉ። ይህም በዘርፉ ኢኮኖሚያዊ ውህደት ያመጣል" ሲሉ በኢጋድ የብሉ ኢኮኖሚ እና የዓሣ ኃብት ከፍተኛ ኤክስፐርት ዋሴ አንተነህ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለዓሣ ሃብት ምርታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ፤ በቀጣናው የዓሣ ምርት እና ንግድን ዘመናዊ ለማድረግ በወጠነው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ከፍተኛ የምክክር መድረክ ላይ ተነስቷል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0