አፍሪካውያን በራሳቸው መንገድ እንዳይሄዱ የቅኝ ግዛት አሻራዎች ተፅዕኖ ፈጥረውባቸዋል - የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአፍሪካውያን በራሳቸው መንገድ እንዳይሄዱ የቅኝ ግዛት አሻራዎች ተፅዕኖ ፈጥረውባቸዋል - የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራር
አፍሪካውያን በራሳቸው መንገድ እንዳይሄዱ የቅኝ ግዛት አሻራዎች ተፅዕኖ ፈጥረውባቸዋል - የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.08.2025
ሰብስክራይብ

አፍሪካውያን በራሳቸው መንገድ እንዳይሄዱ የቅኝ ግዛት አሻራዎች ተፅዕኖ ፈጥረውባቸዋል - የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራር

ቅኝ ግዛት በቁሳዊ እና በአስተሳሰብ ረገድ የፈጠረውን እና የሚያሳድረውን ተፅዕኖ በተመለከት በዛሬው ዕለት ታስቦ የዋለውን የዓለም ወጣቶች ቀን አስመልክቶ ይሁነኝ መሃመድ ሃሳባቸውን ለስፑትኒክ አፍሪካ አካፍለዋል።

"...የቅኝ ግዛት ቋንቋዎች ቋንቋ ብቻ ሳይሆኑ ከቋንቋው ጋር ተያይዞ ደግሞ አረዳድ፣ ግንዛቤ እና አማራጮች፣ አሠራሮቻቸው፣ የመንግሥት አወቃቀራቸው እና ጉዳዮቻቸውን ማስፈፀሚያ ይሆናሉ" ሲሉ ይሁነኝ ይሞግታሉ።

አክለውም አሁን ባለንበት ሁኔታ የአፍሪካ ወጣቶች ወደ ምዕራባውያን ሀገሮች የሚፈልሱበት ምክንያት በአፍሪካ ውስጥ ካለው የሰላም የደህንነት ችግር እንዲሁም የሀገራቸውን እምቅ ችሎታ ካለመረዳት የተነሳ እንደሆነ ያስረዳሉ።

"ሰላማዊ ቦታ ላይ ያለ ማህበረሰብ ተስፋ ይኖረዋል" ሲሉ የሰላም አስፈላጊነት ላይ አፅንኦት ሰጥተዋል።

እንደ ብሪክስ ያሉ አደረጃጀቶች የወጣቶችን አቅም በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አላቸው ብለዋል።

"... እ.ኤ.አ. በ2024 በሩሲያ በተካሄደው የብሪክስ የወጣቶች ምክር ቤት መድረክ ላይ ተሳትፌ ነበር፤ ከውጭ ተጽዕኖዎች ራሳችንን መጠበቅ፣ ፍትሐዊ እድገትን መፈለግ እና ትብብርን ማጎልበት ሁሉም አባል ሀገራት የሚጋሩት እንደሆነ በስብሰባው ወቅት ተገልጿል" ሲል ትብብሩ ለወጣቶች የሚሰጠውን ቦታ አስረድተዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0