"ስትጀምር ትልቁ ፈተና ሐሳብህን የሚደግፍ ማጣት ነው!"

ሰብስክራይብ

"ስትጀምር ትልቁ ፈተና ሐሳብህን የሚደግፍ ማጣት ነው!"

◻ የዊ ኬር የተቀናጀ የጤና አውታረ መረብ መሥራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቤተል ደረጄ፤ ከ4 ዓመታት በፊት የዲጂታል ሕክምና እና ማማከር አገልግሎት ስትጀምር ካሳለፈቻቸው ፈተናዎች ውስጥ እጅግ ከባዱ ለፈጠራ ሐሳቧ ጆሮ የሚሰጣት አካል በቀላሉ አለማግኘቷ መሆኑን ትገልጻለች።

"ሥራውን ለመጀመር የገጠመን ዋነኛው ተግዳሮት ሐሳቡን የሚደግፍ አካል አለማግኘት ነው። በዚህም ማድረግ የምትችለው ብቸኛው ነገር ፈጠራህን የግድ ራስህ ስፖንሰር ማድረግ ነው። ሌላው ደግሞ የዲጂታል የሕክምና አገልግሎትን የተመለከቱ ፖሊሲዎች እና ደንቦች አለመኖራቸው ነበር። በዚህም የት መሄድ እንዳለብን እንኳን አናውቅም ነበር" ስትል ለስፑትኒክ አፍሪካ ጅማሮዋን ተርካለች።

የዊ ኬር የተቀናጀ የጤና አውታረ መረብ አሁን ላይ ከ4 ሺህ ለሚበልጡ የሕክምና ባለሙያዎች የሥራ ዕድል ሲፈጥር፤ በሕክምና ማማከር አገልግሎትም ከ112 ሺህ በላይ ታካሚዎችን ተደራሽ አድርጓል።

ዶ/ር ቤተል ደረጄ ለጀማሪ ስታር አፖች ትምህርት የሚሆኑ ተሞክሮዎቿን አጋርታናለች።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0