ኒጀር የከበሩ ድንጋዮች እና ሜትሮይቶችን ወደ ውጭ ሀገራት መላክ አገደች
20:22 11.08.2025 (የተሻሻለ: 20:24 11.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኒጀር የከበሩ ድንጋዮች እና ሜትሮይቶችን ወደ ውጭ ሀገራት መላክ አገደች
ክልከላውን የፈረሙት ፕሬዝዳንት አብዱራሃማን ቲቺያኒ፤ ዓላማው "የሀገሪቱን የተፈጥሮ ሀብት መጠበቅ፣ መቀነባበራቸውን ማበረታታት እና ዱካቸውን መከታተል ነው" ብለዋል።
እገዳው ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ያልተገለፀ ሲሆን ከፊል ውድ የሆኑ ድንጋዮችንም ያጠቃልላል።
ሆኖም "በሀገሪቱ ጥቅም ላይ በመመሥረት እንደ ሁኔታው" እገዳው ሊነሳ ይችላል ተብሏል።
የኒጀር ባለሥልጣናት 5 ሚሊየን ዶላር በሆነ ዋጋ በኒውዮርክ በጨረታ የተሸጠውን የማርስ ሜትሮይት ጉዳይ አስመልክቶ በነሃሴ ወር ምርመራ መክፈታቸው የሚታወስ ነው። 24.5 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ይህ ሜትሮይት በኒጀር አጋዴዝ ክልል ውስጥ እ.ኤ.አ በ2023 ነበር የተገኘው።
በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X