"ከቀድሞ የሶቪየት ኅብረት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፤ ሀገራቸውን በተለያዩ መስኮች ያገለገሉ ምስጉን ኢትዮጵያውያን ወጥተዋል"
19:40 11.08.2025 (የተሻሻለ: 20:14 11.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"ከቀድሞ የሶቪየት ኅብረት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፤ ሀገራቸውን በተለያዩ መስኮች ያገለገሉ ምስጉን ኢትዮጵያውያን ወጥተዋል"
ይህን ያሉት አንጋፋዎቹ የቀድሞ የሶቪየት ኅብረት ተማሪዎች ዶ/ር ክብሩ ቸርነት እና ዶ/ር ደረጀ ጌታሁን ናቸው።
ዶ/ር ክብሩ ቸርነት በእርሳቸው ጊዜ ሶቪየት ኅብረት 1 ሺህ ለሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ነፃ የትምህርት ዕድል መስጠቷን አስታውሰው ቆይታቸውም ፍሬያማ እንደነበር ገልጸዋል።
በዚህም ሀገሪቱ እ.አ.አ ከ1949 ጀምሮ በኢትዮጵያ የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት ጉዞ ውስጥ ቀላል የማይባል አሻራ ማሳረፏን ተናግረዋል።
በሶቪየት ኅብረት በቬተርነሪ የሙያ መስክ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ዶ/ር ደረጀ ጌታነህ በበኩላቸው፤ ሀገራቱ በተለይ በትምህርት መስክ የነበራቸውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር መሥራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
ዶ/ር ደረጀ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ በአሁኑ ወቅት በሩሲያ ትምህርታቸውን የመከታተል ፍላጎት ላላቸው ወጣቶችም ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X