የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሀብት ፈንድ በአኮቦ የማዕድን ድርጅት የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ፈፀመ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሀብት ፈንድ በአኮቦ የማዕድን ድርጅት የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ፈፀመ
የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሀብት ፈንድ በአኮቦ የማዕድን ድርጅት የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ፈፀመ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.08.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሀብት ፈንድ በአኮቦ የማዕድን ድርጅት የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ፈፀመ

የፈንዱ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በኢትዮጵያ የወርቅ ማውጣት ሥራ ላይ ከተሠማራው የኖርዌው አኮቦ የማዕድን ኩባንያ ሶስት ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያለው 7.4 በመቶ ድርሻ መግዛቱን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ፤ “በአኮቦ ማዕድን የምናደርገው ኢንቨስትመንት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መስፋፋት ታሪካዊ እና ስታራቴጂካዊ እመርታ ነው” ብለዋል፡፡

ውሳኔው ኢትዮጵያ ከክፍለ ዘመን በኋላ ወደ ዓለም አቀፍ የአክስዮን ገበያ እንድትመለስ ያደረገ እና ለቀጣይ የድንበር ተሻጋሪ ኢንቨስትመንቶች በር የከፈተ ነው ሲል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ኢንቨስትመንቱ አኮቦ አዲስ ማዕድን ማውጫ ለመገንባት የሚያስፈልገውን ወጪ የሚደግፍ ሲሆን ይህም የድርጅቱን ወርሃዊ የወርቅ ምርት ከ5-10 ኪሎ ግራም ወደ 50-80 ኪሎ ግራም ከፍ እንደሚያደርገው ይጠበቃል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0