የፍልስጤም የጋዜጠኞች ማህበር እስራኤል በጋዛ በዘጋቢዎች ላይ በምትፈፅመው ጥቃት ዙሪያ ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረበ
15:32 11.08.2025 (የተሻሻለ: 16:34 11.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየፍልስጤም የጋዜጠኞች ማህበር እስራኤል በጋዛ በዘጋቢዎች ላይ በምትፈፅመው ጥቃት ዙሪያ ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረበ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የፍልስጤም የጋዜጠኞች ማህበር እስራኤል በጋዛ በዘጋቢዎች ላይ በምትፈፅመው ጥቃት ዙሪያ ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረበ
የማህበሩ ምክትል ዳይሬክተር ታክሲን አል-አስታል ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በእስራኤል ጥቃት ምክንያት ለተገደሉት አምስት የአልጀዚራ ሠራተኞች ሞት ተጠያቂ የሆኑትን ለፍትሕ እንዲያቀርብ እንጠይቃለን ሲሉ ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡
አልጀዚራ ትናትና ሌሊት በአል-ሺፋ ሆስፒታል አቅራቢያ በሚገኝ ካምፕ ላይ በደረሰ ጥቃት ታዋቂውን ጋዜጠኛ አናስ ጀማል አል-ሸሪፍን ጨምሮ አምስት ሠራተኞቹን እንዳጣ አስታውቋል።
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ጥቃቱን እንደፈፀመ ያረጋገጠ ሲሆን ሟቹን ጋዜጠኛ “ጋዜጠኛ መስሎ የቀረበ አሸባሪ ” ሲል ፈርጆታል። ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ ባሳለፍነው ሐምሌ በጋዜጠኛው ላይ እየደረሰ ያለው ማስፈራሪያ እንዳሳሰበው በመግለፅ፤ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጣልቃ እንዲገባ ጠይቆ ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia
/ © telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየፍልስጤም የጋዜጠኞች ማህበር እስራኤል በጋዛ በዘጋቢዎች ላይ በምትፈፅመው ጥቃት ዙሪያ ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረበ

© telegram sputnik_ethiopia
/