ሩሲያ እና አፍሪካ አማራጭ የክፍያ ስርዓቶችን በመጠቀም የንግድ ግንኙነታቸውን ሊያሳድጉ እንደሚችሉ አምባሳደሩ ገለፁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ እና አፍሪካ አማራጭ የክፍያ ስርዓቶችን በመጠቀም የንግድ ግንኙነታቸውን ሊያሳድጉ እንደሚችሉ አምባሳደሩ ገለፁ
ሩሲያ እና አፍሪካ አማራጭ የክፍያ ስርዓቶችን በመጠቀም የንግድ ግንኙነታቸውን ሊያሳድጉ እንደሚችሉ አምባሳደሩ ገለፁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.08.2025
ሰብስክራይብ

ሩሲያ እና አፍሪካ አማራጭ የክፍያ ስርዓቶችን በመጠቀም የንግድ ግንኙነታቸውን ሊያሳድጉ እንደሚችሉ አምባሳደሩ ገለፁ

በኮትዲቯር የሩሲያ አምባሳደር አሌክሲ ሳልቲኮቭ ይህ እንቅስቃሴ በሩሲያ እና በአፍሪካ መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ በእጅጉ ይጠቅማል ብለው እንደሚያምኑ፤ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ 'ለምዕራባውያን የክፍያ ስርዓቶች አማራጭ የመፈለግ ሃሳብ' ማንሳታቸውን አስመልክቶ ለሩሲያ ሚዲያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ሳልቲኮቭ ሩሲያ ብሔራዊ እና ዲጂታል ገንዘቦችን በተለይም ከብሪክስ ሀገራት ጋር በብዛት ጥቅም ላይ እያዋለች እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ከ 85% በላይ የሚሆነው ከብሪክስ አባል ሀገሮች ጋር የሚደረግ የንግድ ልውውጥ በብሔራዊ ገንዘቦች እንጂ በዶላር አይፈጸምም።

ሩሲያ የ "ስዊፍት" አማራጭ የሆነውን "ፋይናሻል ሜሴጅ ትራንስፈር ሲስተም" የተሰኘውን የክፍያ ስርዓቷን እያሰፋች ነው።

"የአፍሪካ ሀገራትም እንደ ዶላር፣ ዩሮ ወይም ፓውንድ ስተርሊንግ ካሉ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ስርዓቶች ነጻ የሆኑ የክፍያ ዘዴዎችን ለመዘርጋት ይፈልጋሉ፡፡ እስካሁን ባለኝ መረጃ አስር የአፍሪካ ሀገሮች ይህን ስርዓት ለመዘርጋት በትብብር እየሠሩ ነው። በአፍሪካ ውስጥ ያለው የእርስ በእርስ የንግድ ልውውጥ ከፍተኛ ነው" ሲሉም አክለዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0