ግብጽ 13 የተሰረቁ ቅርሶችን ከብሪታንያ እና ከጀርመን አስመለሰች
18:10 10.08.2025 (የተሻሻለ: 18:14 10.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ግብጽ 13 የተሰረቁ ቅርሶችን ከብሪታንያ እና ከጀርመን አስመለሰች
እነዚህ ውድ ቅርሶቹ ከግብጽ በሕገ-ወጥ መንገድ የወጡ ሲሆን መመለሳቸውም መንግሥትን ቅርስ ለመጠበቅ እና ለማስመለስ እያደረገ ያለው ጥረት አካል ነው ሲል የቱሪዝም እና ቅርሶች ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል።
የተመለሱት ቅርሶች፦
🟠 "ባሴር" የተባለውን የግንባታ ሥራ ተቆጣጣሪ የሚያሳይ የኖራ ድንጋይ የሬሳ ሳጥን (የመጨረሻው ጥንታዊ የግበፅ ዘመን)፣
🟠 የአንገት ምልክት ክታብ፤ የጥንታዊውን የግብጽ ባሕል ሕይወትን የሚወክል፣
🟠 ማንነቱ ያልታወቀ መሚ የራስ ቅል እና ክንድ፤
🟠 በዶቃ ያጌጠ የሬሳ ማስክ እና ሌሎችም ይገኙበታል።
ሁሉም ቅርሶች ለግብጽ ሙዚዬም የተሰጡ ሲሆን በቅርቡ ለተመለሱ ቅርሶች ልዩ ኤግዚቢሽን ላይ ለእይታ እንደሚቀርቡ ሚኒስቴሩ አክሎ ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X




