የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት የገዥውን ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ አስጀመሩ
16:52 10.08.2025 (የተሻሻለ: 16:54 10.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት የገዥውን ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ አስጀመሩ
ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን ከምርጫ ኮሚሽኑ የእጩ ቅፅ በመቀበል የምርጫ ዘመቻውን በይፋ ከፍተዋል ሲል ቻማ ቻ ማፒንዱዚ (ሲሲኤም) ፓርቲ አስታውቋል።
"በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ቪዥን 2050ን ስናስፈጽም ከዚህም በላይ ታላላቅ ምዕራፎችን እናሳካለን…ይህ ምርጫ የግል ወይም የሲሲኤም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን የሁሉም ታንዛኒያውያን ነው። ዜጎች የተከበረ እና የዘላቂ ኢኮኖሚ እውነተኛ እቅድ ያለው ፓርቲ የሚመርጡበት ጊዜ ነው" ብለዋል ሲል የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።
ፕሬዝዳንቷ የሲሲኤም ፓርቲ "በከፍተኛ ልዩነት እንዲያሸንፍ" ሁሉም እንዲያብር አሳስበዋል።
የሲሲኤም ምክትል ሊቀመንበር ስቲቨን ዋሲራ በበኩላቸው "1 ሺህ እጩዎችም ቢወዳደሩ ሲሲኤም የሚፈራው ነገር የለም" ሲሉ ተናግረዋል።
የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳ ከነሃሴ 22 እስከ ጥቅምት 20 የሚቆይ ሲሆን ምርጫው ጥቅምት 21 ይካሄዳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
