የቅኝ ግዛት ውርስ በአፍሪካ የተፈጥሮ ሃብት ብዝበዛን እንዳስቀጠለ የማዕድን ባለሙያው ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየቅኝ ግዛት ውርስ በአፍሪካ የተፈጥሮ ሃብት ብዝበዛን እንዳስቀጠለ የማዕድን ባለሙያው ተናገሩ
የቅኝ ግዛት ውርስ በአፍሪካ የተፈጥሮ ሃብት ብዝበዛን እንዳስቀጠለ የማዕድን ባለሙያው ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.08.2025
ሰብስክራይብ

የቅኝ ግዛት ውርስ በአፍሪካ የተፈጥሮ ሃብት ብዝበዛን እንዳስቀጠለ የማዕድን ባለሙያው ተናገሩ

አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ማዕድናት በቀጥታ ወደ ቀድሞ ቅኝ ገዢ ሀገራት በተለይም ወደ ብሪታንያ ወይም ፈረንሳይ እንደሚጋዙ የማዕድን ዘርፍ ባለሙያው መስፍን ጌታቸው ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልፀዋል።

"በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እንደ ኮባልት፣ መዳብ እና ወርቅ የመሳሰሉ ማዕድናት የአካባቢውን ሕዝብ ሳይጠቅሙ በተዘዋዋሪ መንገድ ይዘረፋሉ" ያሉት ባለሙያው፤ አፍሪካውያን ሀብታቸውን ሊቆጣጠሩ ይገባል ብለዋል።

ባለሙያው ሀገራት ከማዕድን ዘርፍ መጠቀም እንዲችሉ መፍትሄዎችንም ጠቁመዋል፦

ቀጣናዊ ውህደትን ማጠናከር፣

ዲጂታል እና አረንጓዴ ቴክኖሎጂዎችን መከተል፣

ቁልፍ መሠረተ ልማቶችን መገንባት፣

የሀገር ውስጥ የካፒታል ገበያዎችን ማቋቋም።

"የማዕድን ዘርፍ በውጭ ኩባንያዎች ቁጥጥር ስር ነው። አፍሪካ ከአስተዳደር፣ ከባለቤትነት እና ከልምድ ውጪ ሆናለች። ይህ አፍሪካ ከቅኝ ገዢዎቹ የወረሰችው ነው።"

አክለውም የቅኝ ግዛት ሕጎች ለመንግሥት ወይም ለማሕበረሰብ መብቶች ሳይሆን ለውጭ ኢንቨስትመንት ጥበቃ ቅድሚያ እንደሚሰጡ ጠቁመዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0