የቀድሞው የቻድ ጠቅላይ ሚኒስትር የ20 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው
14:55 10.08.2025 (የተሻሻለ: 15:04 10.08.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የቀድሞው የቻድ ጠቅላይ ሚኒስትር የ20 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው
የተቃዋሚው ፓርቲ ‘ዘ ትራንስፎርመርስ’ መሪ ሱኬ ማሳራ በተጨማሪም 1 ቢሊየን ፍራንክ (1.78 ሚሊየን ዶላር) ቅጣት እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል ሲል ፓርቲያቸው ገልጿል።
የንጃሜና ፍርድ ቤት፦
በግድያ ተባባሪነት እና
በግንቦት ወር በተከሰተው እና ለ42 ሰዎች ሕይወት መጥፋት ምክንያት በሆነው የእርስ በርስ ግጭት የጥላቻ እና መጤ ጠል መልዕክቶችን በማሠራጨት ጥፋተኛ ብሏቸዋል።
የፍርድ ሂደቱ ረቡዕ ዕለት በሁለት ክፍሎች ተከፍሎ መጀመሩን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
▪ግንቦት ላይ የተፈፀመውን የጅምላ ግድያ ፈፅመዋል ተብለው ክስ በቀረበባቸው 70 ሰዎችና፣
▪ግድያውን አነሳስተዋል በተባሉት ማሳራ ላይ የተከፈተ ነበር።
ማሳራ ፍርዱ ሲነገር "የቀረቡብኝን ክሶች አልቀበልም" እንዳሉ ተዘግቧል። ጠበቆቻቸው ለፍርድ ቤቱ ውሳኔ ይግባኝ እንደሚጠይቁ ተገልጿል።
ℹ ማሳራ እ.ኤ.አ በ2022 ከተሰደዱ በኋላ በቀጣይ ዓመት ተመልሰው በፕሬዝዳንት ማህመት ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት ቢያገኙም ያገለገሉት ለአምስት ወራት ብቻ ነበር። በ2024ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተወዳድረው በወቅቱ ፕሬዝዳንት ተሸንፈዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X