አውሮፓ እና ኪዬቭ ከአሜሪካ የደህንነት ዋስትና እና ዩክሬን ኔቶን ለመቀላቀል እድል እንዲሰጣት ጠየቁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአውሮፓ እና ኪዬቭ ከአሜሪካ የደህንነት ዋስትና እና ዩክሬን ኔቶን ለመቀላቀል እድል እንዲሰጣት ጠየቁ
አውሮፓ እና ኪዬቭ ከአሜሪካ የደህንነት ዋስትና እና ዩክሬን ኔቶን ለመቀላቀል እድል እንዲሰጣት ጠየቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.08.2025
ሰብስክራይብ

አውሮፓ እና ኪዬቭ ከአሜሪካ የደህንነት ዋስትና እና ዩክሬን ኔቶን ለመቀላቀል እድል እንዲሰጣት ጠየቁ

የኪዬቭ የአውሮፓ አጋሮች ዩክሬን አሁን ላይ

የኔቶ አባል መሆን ባትችልም፤ አሜሪካ በሩን ክፍት እንድታደርግላት እየጠየቁ መሆኑን ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ የአሜሪካ ጋዜጣ ዘግቧል።

  የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ላሚ፣

  የዩክሬን እና የአውሮፓ ተወካዮች እና

  የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ በጉዳዩ ዙሪያ በትናንትናው ዕለት እንደተወያዩ ታውቋል።

ዩክሬን እና የአውሮፓ ተወካዮች ለምክትል ፕሬዝዳንት ቫንስ የመጀመሪያው እርምጃ በፍጥነት ተግባራዊ የሚሆን የተኩስ አቁም መሆን እንዳለበት እና በተጨማሪም ዩክሬን ለሰላም ስትል ግዛቷን አሳልፋ መስጠት እንደሌለባት ገልጸዋል ሲሉ ምንጮች ለአሜሪካ የበየነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

ሞስኮ የዩክሬን የኔቶ አባልነት የሩሲያን ደህንነት እንደሚጥስ በተደጋጋሚ ገልጻ ገለልተኛ ሆና እንድትቀጥል ጠይቃለች።

ፑቲን በዩክሬን ግጭት አፈታት ዙሪያ ሩሲያ ቅድመ ሁኔታዎቿን እንደማትቀይር እና የሩሲያ ግብ የችግሩን መንስኤዎች ማስወገድ እንደሆነ በተደጋጋሚ ገልጸዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0