የእስራኤል ጋዛን የመቆጣጠር ዕቅድ "የፍልስጤማውያንን የማይገሰስ መብት ይጥሳል" ሲል የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ
12:42 10.08.2025 (የተሻሻለ: 12:44 10.08.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየእስራኤል ጋዛን የመቆጣጠር ዕቅድ "የፍልስጤማውያንን የማይገሰስ መብት ይጥሳል" ሲል የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የእስራኤል ጋዛን የመቆጣጠር ዕቅድ "የፍልስጤማውያንን የማይገሰስ መብት ይጥሳል" ሲል የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ
"የእስራኤል ጽዮናዊ መንግሥት የጋዛን ሰርጥ የመቆጣጠር ዕቅድ አጥብቀን እናወግዛለን፤ በፍልስጤም ሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ያባብሳል" ብሏል።
ኩባ እንደሌሎች የላቲን አሜሪካ ሀገራት ሁሉ ፍልስጤምን ትደግፋለች እንዲሁም በ1967 ድንበር መሠረት ምስራቅ እየሩሳሌምን ዋና ከተማ ያደረገ እውቅና እንድታገኝ ትሟገታለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እስራኤል የጋዛን ሰርጥ ለመቆጣጠር ማቀዷን ሐሙስ ገልጸው ነበር። የእስራኤል የደህንነት ካቢኔ ይህንን ሃሳብ አጽድቋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ሩሲያ፣ ግብፅ፣ ቬንዙዌላ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ኳታር እና ሌሎችም በርካታ ሀገራት የእስራኤልን ውሳኔ አጥብቀው ተቃውመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X